ከዛሬው የዓለማችን የበይነ መረብ ጥቃት ጀርባ ያለው ክራውድ ስትራይክ ማን ነው?
ክራውድ ስትራይክ በተባለው ሶፍትዌር ላይ በደረሰ ጥቃት የበርካታ ሀገራት ተቋማት ስራ ቆሟል
85 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ክራውድ ስትራይክ መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው
ከዛሬው የዓለማችን የበይነ መረብ ጥቃት ጀርባ ያለው ክራውድ ስትራይክ ማን ነው?
ዋና መቀመጫውን ኦስቲን ቴክሳስ ያደረገው ክራውድ ስትራይክ የተሰኘው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ግዙፍ የዓለማችን ተቋማት ያለምንም ስጋት ስራቸውን እንዲሰሩ የሚያደርግ ሶፍትዌር ነበር፡፡
ከየትኛውም ተቋም ሆነ ሀገራት የሚቃጡ የበይነ መረብ ጥቃቶችን በማክሸፍ የሚታወቀው ክራውድ ስትራይክ ሶፍትዌር የበርካታ ሀገራት አየር መንገዶች፣ ባንኮች፣ ሚዲያዎች እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ደንበኞች ናቸው፡፡
በመላው ዓለም ከ29 ሺህ በላይ ተቋማት ደንበኞች ያሉት ይህ ኩባንያ የበይነ መረብ ጥቃቶችን መከላከል ዋነኛ ስራው ቢሆንም በዛሬው ዕለት ራሱ ክራውድ ስትራይክ በደረሰበት ጥቃት በርካታ ተቋማት ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል፡፡
የጡንቻዎቻችንን እንቅስቃሴ ወደ ንግግር የሚቀይር ቴክኖሎጂ ተሰራ
በፈረንጆቹ 2011 የተመሰረተው ክራውድ ስትራይክ ከ170 በላይ ሀገራት እየተጠቀሙት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ጎግልን ጨምሮ አማዞን፣ ኢንቴል እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የሚፎካከረው ክራውድ ስትራይክ የደረሰበት ጥቃት ምንጩ እስካሁን ይፋ አልሆነም፡፡
ሌላኛው የበይነ መረብ ጥቃት ሰለባ የሆነው ማይክሮሶፍት ችግሩን በተወሰነ መልኩ መፍታቱን ቢገልጽም እስካሁን በይፋ የችግሩ ምንጭ አልታወቀም፡፡
ኩባንያው ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 900 ሚሊዮን ዶላር ማትረፉን ገልጾ የነበረ ሲሆን ዛሬ በደረሰበት ጥቃት ምክንያት የአክስዮን ዋጋው በመቀነስ ለይ ይገኛል፡፡
በበርካታ የዓለማችን ሀገራት በክራውድ ስትራይክ ሶፍትዌር ላይ በደረሰው ጥቃት አገልግሎቶች የተቋረጡ ቢሆንም ሩሲያ እስካሁን ምንም አይነት ችግር እንዳልደረሰባት አስታውቃለች፡፡