ከአስሩ ቀዳሚ ባለጠጎች ውስጥም ዘጠኙ አሜሪካውያን መሆናቸውን የብሉምበርግ መረጃ ያሳያል
አለማችን በ2024 2 ሺህ 640 ቢሊየነሮች አሏት።
ከነዚህ ባለጠጎች ውስጥም 735ቱ አሜሪካውያን መሆናቸውን ነው ፎርብስ ያወጣው ዘገባ የሚያሳየው።
ብሉምበርግ በትናንትናው እለት ይፋ ያደረገው የቢሊየነሮች ደረጃም ይህንኑ የሚያሳይ ነው።
ከአስሩ የምድራችን ሃብታሞች ዘጠኙ አሜሪካውያ ናቸው፤ አብዛኞቹም በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ናቸው።
የአማዞን መስራቹና ቁጥር አንድ ባለጠጋ ጄፍ ቤዞስን ጨምሮ ኤለን መስክ፣ ቢል ጌትስ፣ ማርክ ዙከርበርግ እና ሌሎች ቢሊየነሮች በቴክኖሎጂው ዘርፍ ፈር ቀዳጅ መሆናቸው ይታወሳል።
ቴክኖሎጂ ቢሊየነር ያደረጋቸው አሜሪካውያን በፈጠራ ውጤታቸው ላይ ለደቂቃ እና ስአታት የሚገጥም ችግር ቢሊየን ዶላሮችን የሚያሳጣ መሆኑም በትናንትናው እለት ሜታ የገጠመው ትልቅ ማሳያ ነው።
ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ትሪድስ ለሁለት ስአት መስራት አስቸግሮ ሜታ ከ20 ቢሊየን ዶላር በላይ ማጣቱ ተዘግቧል።
የብሉምበርግ እስከ መጋቢት 5 2024 ባለው ጊዜ የአለማችን 10ሩ ባለጠጎች ደረጃን ቀጥሎ ቀርቧል፦