ዋትስአፕ በድምጽ የተላከ መልእክትን ወደ ጽሁፍ የሚቀይር አገልግሎት ስራ ላይ ሊያውል ነው
አዲሱ አገልግሎት በተለይም ድምጽ ለማስማት አመቺ ባልሆነ ስፍራዎች ለይ ስንሆን ጠቃሚ ነው ተብሏል
አግልግሎቱ በቅርቡ ለአይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተጠቃሚዎች ይለቀቃል ነው የተባለው
የጽሁፍ፣ ድምጽ፣ የፎቶ ግራፍ እና ተንቀሳቃሽ ምስል መላላኪያ የሆነው የማህበራ ትስስር ገጹ ዋትስአፕ አዲስ አገልግሎት ይዤ እየመጣሁ ነው ብሏል።
አዲሱ የዋትስአፕ አገልግሎት በድምጽ የተላከ መልእክትን ወደ ጽህፉ የሚቀይር ነው የተባ ሲሆን፤ ለአይፎን (አይ.ኦ.ኤስ) ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተጠቃሚዎች በቅርቡ ይለቀቃል መባሉን ፎሲባይተስ የተባ የቴክኖሎጂ ድረ ገጽ አስነብቧል።
አሁን ላይ እየለማ ነው የተባለው አዲሱ የዋተስአፕ አግልግሎት በቅርቡ በዋስአፕ ቤታ አማካኝነት በአፕ ስቶር ላይ እንደሚለቀቀም ነው የተገለፀው።
አዲሱ የዋትስአፕ አገልግሎት በቅድሚያ ለአይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተጠቃሚዎች ይለቃል የተባለ ሲሆን፤ የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ስልክ ተጠቃሚዎች እስከዚያው እንደ ትራንስክራይበር ያሉ መተግበሪያዎችን በማውረድ ሊጠቀሙ ይችላሉ ተብሏል።
ከቆይታ በኋላም የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተጠቃሚዎች አዲሱን አግለግሎት በዋትስአፕ አፕዴት በኩል ሊያገኙ ይችላሉ ነው የተባለው።
አዲሱ የዋትስአፕ አገልግሎት በተለይም ድምጽ ለማስማት አመቺ ባልሆነ ስፍራዎች ለይ ስንሆን በድምጽ የተላከልንን መልእክተ ወደ ጽሁፍ ቀይረን እንድናነብ በማድረግ ረገድ ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ተብሏል።