ዋትስአፕ የአሰራር ሂደታቸውን ወደ iOS 9 እና Android 4.0.3. ባላዘመኑ ስልኮች ላይ መስራት አቁሟል ተብሏል
የሚድያዎች ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከሆነ፡ በዋትስአፕ መልእክት ለመላክ የሚስችል መተግበርያ በተወሰኑ ዘመናዊ ስልኮች ላይ አገልግሎቱን የሚያቆም ይሆናል፡፡
መልእክት ለመላክ የሚያስችል መተግበርያው ፤በቆዩ አይፎኖች አንደማይሰራም ነው የWABetaInfo. ሪፖርት ያሳወቀው፡፡ በiOS 9ን ለሚያሄዱ መሣሪያዎች ድጋፍ የሚሰጠው የ iOS መተግበሪያ የቅርብ ጊዜ የቤታ ስሪት እንደሆነና ቀደም ሲል ከጥቅም ውጭ መሆኑ ያስታወሰው ሪፖርቱ፤ በዌብሳይቱ ላይ የሰፈሩት የመተግበርያ መረጃዎችን የተመለከተ እስካሁን የተረጋገጠ ነገር እንደሌለ ተገጿል፡፡
አሁን ላይ በመልእክት መተግበርያው ፕሮግራም ሊሰራ የሚችል አይፎን ቢኖር፤ iOS 9 ነው ተብሏል፡፡ የመልእክት መተግበርያው ካለፈው ጥር 1 ጀምሮ በተለያዩ መሳርያዎች፤ በተለይም የአሰራር ሂደታቸውን ወደ iOS 9 እና Android 4.0.3. ባላዘመኑ ሰዎች ላይ መስራት እንዳቆመም በሪፖርቱ ተካተዋል፡፡