ፌስቡክ ከሬይ ባን ኩባንያ ጋር በጋራ የሰራው መነጽር ለገበያ ሲቀርብ 300 ዶላር መሸጫ ዋጋ ተቆርጦለታል
ፌስቡክ ኩባንያ ፎቶግራፍ ማንሳት እና ቪዲዮ መቅረጽ የሚችል ካሜራ የተገጠመለት መነጽር ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል።
አዲሱ ባለካሜራው የፌስቡክ መነጽር ከመነጽር አምራቹ “ሬይ ባን” ኩባንያ ጋር በጋራ በመሆን የተሰራ ሲሆን፤ ለገበያ በሚቅርብበት ጊዜም በ300 ዶላር ይሸጣል ተብሏል።
- ኢትዮጵያ ፌስቡክንና ትዊተርን በሀገራዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የመተካት እቅድ እንዳላት አስታወቀች
- ፌስቡክ በኢትዮጵያ እና ኬንያ የፖለቲካ ይዘት ባላቸው ማስታወቂያዎች ላይ ቁጥጥር ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ
አዲሱ የፌስቡክ ባለካሜራ መነጸር ስልካችንን ከኪሳችን ማውጣት ሳያስፈልገን ፎቶ ግራፍ ማሳት እና ቪዲዮ መቅረጽ የሚያስችል ሲሆን፤ በመነጸሩ ሌንስ ላይ ሙዚቃ ማጫወት እና ማዳመጥ የሚያስችል ነው ተብሏል።
መነጽሩ ላይ እያንዳንዳቸው 5 ሜጋ ፒክስል የሆኑ ሁለት የካሜራ ሌንሶች በግራ እና በቀኝ የተገጠሙ ሲሆን፤ ሁለቱም አንድ ላይ በመሆን 10 ሜጋ ፒክስልለ ጥራት ያለው ፎቶግራፍን ማንሳት ይችላሉ።
መነጽሩ ላይ የተገጠመው ካሜራ 12 ሜጋ ፒከስል ያላቸው ስልኮች ከሚያነሱት ጋር ተመሳሳይ ጥራት ለው ፎቶግራፍ ማሳት እንደሚችልም የዋሽንግተን ፖስት ዘገባ ያመለክታል።
ካራው የሚቀርጻቸው ቪዲዮዎችም ቢሆኑ ጥሩ የሆን ጥራ አላቸው የተባለ ሲሆን፤ በተለይም ለቲክቶክ እና ኢኒስታግራም የሚሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለመቅረጽ ያስችላል።
ሆኖም ግን በመነጽሩ በአንድ ጊዜ መቅረጽ የሚቻለው 30 ሰከንድ ርዝመት ያለው ቪዲዮ ብቻ ነው ተብሏል።
ፌስቡክ ኩባንያ ካሜራ የተገጠመለት መነጽሩን አሁን ላይ ለእይታ ያቀረበ ሲሆን፤ በቅርቡ በስፋ ተመርተው ለገበያ እንደሚቀርብም አስታውቋል።