የአለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ የህብረተሰብ ጤና ስጋት ሆኗል ሲል ለሁለተኛ ጊዜ አወጀ
በሽታው ከኮንጎ ወደ ሌሎች ጎረቤት ሀገራት መሰራጨቱ የአለምጤና ድርጅት እርምጃ እንዲወስድ አስገድዶታል
ዶክተር ቴድሮስ "እነዚህን ወረረሽኞች ለማስቆም እና ህይወት ለማዳን የተቀናጀ አለምአቀፋዊ ምላሽ ለመስጠት አስፈላጊ ሆኗል" ብለዋል
የአለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ የህብረሰብ ጤና ስጋት ሆኗል ሲል ለሁለተኛ ጊዜ አወጀ።
የአለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ መከሰቱን እና ወደ ጎረቤት ሀገራት መስፋፋቱን ተከትሎ በሁለት አመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በሽታው አለምአቀፋዊ የህብረተሰብ ጤና ስጋት መሆኑን አውጇል።
የአስቸኳይ ጊዜ ኮሚቴ በሽታው የህብረተሰብ ጤና ስጋት መሆኑን ወይም አለመሆኑን ለድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ለማማከር ባለፈው ረቡዕ እለት ስብሰባ አድርገው ነበር።
የህብረተሰብ ጤና ስጋት ደረጃ፣ ድርጅቱ የሚሰጠው ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ሲሆን ይህም በበሽታው ዙሪ ጥናት እና እርዳታ እንዲፋጠን እንዲሁም በሽታውን ለመቆጣጠር አለምአቀፋዊ የህብረተሰብ ጤና እርምጃዎችን ለመውሰድ ያለመ ነው።
"እነዚህን ወረረሽኞች ለማስቆም እና ህይወት ለማዳን የተቀናጀ አለምአቀፋዊ ምላሽ ለመስጠት አስፈላጊ ሆኗል" ብለዋል ዶክተር ቴድሮስ።
የዝንጅሮ ፈንጣጣ በንክኪ የሚተላለፍ በሽታ ነው። ብዙ ጊዜ ቀላል የሚባል ቢሆንም አልፎአልፎ እስከሞት የሚያደርስ ነው። በሽታው የጉንፋን አይነት ምልክቶችን እና በሰውነት መግል የያዙ ትናንሽ እብጠቶችን ያስከትላል።
በኮንጎ የተሰራጨው ወረርሽኝ ልዩ መጠሪያው ወይም ዝርያ ክላድ አይ ተብሎ ይጠራል። ነገርግን ክላድ አይቢ የተባለው አዲሱ ዝርያ በወሲባዊ ግንኙነት ጨምሮ በቀላሉ የሚተላለፍ ነው ተብሏል።
በሽታው ከኮንጎ ወደ ቡሩንዲ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ እና ወደ ሌሎች ጎረቤት ሀገራት መሰራጨቱ የአለምጤና ድርጅት እርምጃ እንዲወስድ አስገድዶታል።
ዶክተር ቴድሮስ የአዲሱ የበሽታው ዝርያ በፍጥነት መስፋፋት እና ከዚህ ቀደም ባልታየባቸው ጎረቤት ሀገራት መከሰት እንዲሁም በአፍሪካ ውስጥ የመስፋፋት አቅሙ እንደሚያስጨንቃቸው ገልጸዋል።
ድርጅቱ ለአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ለመስጠት 1.5 ሚሊዮን መመደቡን እና በመጭዎቹ ቀናት ተጨማሪ እንደሚለቅ ተናግረዋል ዳይሬክተሩ። የድርጀቱ የመጀመሪያ ምላሽ እቅድ 15 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈገው ተገልጿል።
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የአፍሪካ ከፍተኛ የህብረተሰብ ጤና አካል የዝንጀሮ ፈንጣጣ የአህጉሪቱ አደጋ ሲል አውጇል። በሽታው በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ሲሆን ቢዚህ አመት ህጻናትን ጨምሮ 500 ሰዎች ሲሞቱ፣ 17ሺ የሚሆኑ ደግሞ በሽታው ሳይዛቸው አይቀርም ተብሎ ተጠርጥረዋል።