ሳይንቲስቶቹ እንገለጹት እያንዳንዷ ላም በማግሳት በአመት ከ70 እስከ 120 ኪሎግራም የሚሆን የሚቴን ጋዝ ወደ ከባቢ አየር ትለቃለች
ላሞች እና እንስሳት ከፍተኛ መጠን ያለው ሚቴን ወደ ከባቢ አየር ይለቃሉ።
ሳይንቲክቶች ቀይ አልጌን በመጠቀም የአየር ብክለት እንዲቀንስ ለማድረግ በጥረት ላይ ናቸው።
እያንዳንዷ ላም በማግሳት በአመት ከ70 እስከ 120 ኪሎግራም የሚሆን የሚቴን ጋዝ ወደ ከባቢ አየር ትለቃለች። ሚቴን ለከባቢ አየር መቁት መጠን መጨመር 30 በመቶ ድረሻ ያለው ሲሆን ለዚህም ላሞች እና የቁም እንስሳት ከፍተኛ አበርክቶ አላቸው። ሰዎች ስጋን ዘወትር ከመመገብ እንዲቆጠቡ የሚመክሩ በርካታ ሀሳቦች ቢወጡም ሰዎች የሚወዱትን ስጋ እንዳይጠቀሙ ማድረግ አልቻሉም።
አካባቢን ሳንጎዳና እና ሚቴን ወደ ከባቢ አየር ሳንለቅ ስጋን እንዴት መመገብ እንችላለን?
የስዊድን ኡፕሳላ ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶች በዚህ ጉዳይ ምርምር አድርገዋል።በምርምራቸውም የተወሰኑ የቀይ አልጌ ዝርያዎች ከላም የሚወጣውን የሚቴን ጋዝ መጠን መቀነስ እንደሚችሉ አረጋግጠዋል።
ትንሹ ቀይ አልጌ
ሳይንቲስቶች በሳይንሳዊ ስያሜው አስፕራጎፕሲስ ታክስፎሪምስ የባለውን እና በትሮፒካል የውሃ አካላት ላይ የሚበቅለውን ትንሹን ቀይ አልጌ ዝርያ ጥቅም ላይ አውለዋል።
ይህ አልጌ የእንሳሳት ጽዳጅ የሚለቀውን የጋዝ መጠን በግማሽ እንደሚቀንስ ሳይንቲስቶች አረጋግጠዋል።
እንደ ሳይንቲስቶቹ ጥናት እነዚህ አልጌዎች ብሮሞፎርም በተባለው ቁሳቸው አማካንነት የሚቴን ጋዝ እንዳይፈጠር ያደርጋሉ።