የአየር ንብረት ለውጥ የሚቋቋሙ ግንባታዎች ላይ በማተኮር፣ ዘርፉ የሚለቀቀውን 40 በመቶ ብክለት መቀነስ ይቻላል- ተመድ
የግንባታው ዘርፍ 37 በመቶ ለሚሆነው የአየር ብክለት ምክንያት መሆኑን ተመድ ገልጿል
ሪፖርቱ እንደገለጸው መንግስታት የካርበን ልቀታቸው ከፍተኛ የሆኑ የግንባታ እቃዎች ጥቅም ላይ እንዳይዉሉ ፖሊሲ ማውጣት አለባቸው
ተመድ ይፋ ባድገው ሪፖርት የአየር ብክለትን የሚቋቋም ግንባታ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ ጉልህ ሚና ይኖረዋል።
እንደሪፖርቱ ከሆነ የአየር ንብረት ለውጥ የሚቋቋሙ ግንባታዎች ላይ በማተኮር፣ በ2050 በዘርፍ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን 40 በመቶ ብክለት መቀነስ ይቻላል።
የተመድ የአካባቢ ፕሮግራም ይፋ ባደረገው 'የግንባታ እቃዎች እና ከባቢ አየር- መጭውን ጊዜ መገንባት' ሪፖርቱ ላይ አሁን ላይ ባለው የከተማ መስፋፋት በአየምስት ቀናቱ የፖሪስን ህንጻች ያህል ቁጥር ያላቸው ግንባታዎች ይገነባሉ።
የግንባታው ዘርፍ 37 በመቶ ለሚሆነው የአየር ብክለት ምክንያት ሆኗል።
ከቤል ሴንተር ፎር ኢንቫይሮንመት ሲስተም እና ግሎባል አሊያንስ ፎር ኮንስትራክሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ጥናት፣ በግንባት እቃዎች የሚደርሰው ብክለት እንዲቀንስ እና የግንባታ እቃዎችን በድጋሚ ጥቅም ላይ ማዋል እና ታዳሽ ኃይልን በመጠቀም በዘርፉ የሚደርሰውን ብክለት ከ50 እስከ 75 በመቶ እንዲቀንስ ጥሪ አቅርቧል።
ሪፖርቱ ለግንባታ አነስተኛ ግብአቶችን መጠቀም፣ ብክለትን የሚቋቋም ዲዛይን እና ድጋሚ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ግብአቶችን መጠቀም የብክለት መቀነሻ ዘዴዎች መሆናቸውን ጠቅሷል።
በድጋሚ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ግብአቶችን በጥናት መለየት አስፈላጊ ነው ብሏል ሪፖርቱ።
ዝቅተኛ ካርበን ልቀት እንዲኖር፣ የግንባታ እቃዎች እንዴት ጥቅም ላይ ይዋሉ እና ምንጫቸው ምን ይሁን በሚለው ላይ ለውጥ ያስፈልጋል ያለው ሪፖርቱ ታዳሽ ያልሆነ የኃይል ምንጭን ከመጠቀም ይልቅ ታዳሽ ምንጭ ላይ ማተኮር ያስፈልጋል ብሏል።
ሪፖርቱ እንደገለጸው መንግስታት የካርበን ልቀታቸው ከፍተኛ የሆኑ የግንባታ እቃዎች ጥቅም ላይ እንዳይዉሉ ፖሊሲ ማውጣት አለባቸው።