የአባቷን ገዳይ ለመያዝ የፖሊስ አባል የሆነችው እንስት ከ25 አመታት በኋላ ገዳዩን በቁጥጥር ስር አዋለች
ከግድያው በኋላ እራሱን ደብቆ በሽሽት ላይ የነበረው ግለሰብ ወንጀለኛውን ለመያዝ የእድሜ ልክ እቅድ በነበራት የሟች ልጅ በህግ ስር ውሏል
በጊዜው የ9 አመት እና የቤተሰቡ የመጀመርያ ልጅ የሆነችው ታዳጊ ለአመታት በፍትህ ማጣት ሲብሰለሰሉ የኖሩ ቤተሰቦቿ ሁኔታ በአዕምሯ ውስጥ ተቀርጾ አደገች
አባቷን ገዳይ በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስን የተቀላቀለችው ብራዚላዊት እንስት ከ25 አመታት በኋላ ገዳዩን በቁጥጥር ስር አውላለች፡፡
ጥር 16፣ 1999 ከዛሬ 25 አመት በፊት ቦአ ቪስታ በተባለ የብራዚል ከተማ ውስጥ በሚገኝ መጠጥ ቤት ውስጥ በተፈጠረ ግጭት ጊቫልዶ ጆሴ ቪሴንቴ የተባለው ሰው በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ያልፋል፡፡
ሬይሙንዶ አልቬስ የተባለው ግድያውን የፈጸመው ግለሰብ ሟቹ የነበረበትን 150 ሪልስ የብራዚል ገንዘብ መልስልኝ በሚል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ግጭት ያድጋል፡፡
ቀጥሎም ገዳዩ መጠጥ ቤቱን ትቶ ከወጣ ከጥቂት ቆይታዎች በኋላ ሽጉጥ ታጥቆ በመምጣት የአምስት ልጆች አባት የሆነውን ጊቫልዶ ቬሴንቶ ጭንቅላቱ ላይ ተኩሶ ገድሏል፡፡
በወቅቱ በአፋጣኝ ከአካባቢው የተሰወረው ገዳይ በስሙ የፖሊስ ማደኛ ቢወጣበትም ፖሊስ የተለያዩ ክትትል እና ማጣርያዎችን ቢያደርግም ሊይዘው አልቻለም፡፡
በጊዜው የ9 አመት እና የቤተሰቡ የመጀመርያ ልጅ የሆነችው ታዳጊ ለአመታት በፍትህ ማጣት ሲብሰለሰሉ የኖሩ ቤተሰቦቿ ሁኔታ በአዕምሯ ውስጥ ተቀርጾ አደገች፡፡
ጂስሊየን ሲልቫ ዴዲውስ የተባለችው ብራዚላዊት የአባቷን ሞት ተከትሎ አምስት ልጆችን ለማሳደግ ሀላፊነት የወደቀባትን እናቷን ለማገዝ የተለያዩ ስራዎችን ሰርታለች፡፡
ሆኖም ጎን ለጎን ትምህርቷን መከታተል እና የምንግዜም ህልሟ የሆነውን የአባቷን ገዳይ ለፍትህ የማቅረብ ጉዳይ ዘንግታ አታውቅም፡፡
በ8 አመቷ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ከተመረቀች በኋላ ህግ በማጥናት ለ7 አመታት ጠበቃ ሆና አገልግላለች፡፡
በ2022 የጥብቅና ስራዋን በመተው የአባቷን ገዳይ ለመያዝ ፖሊስን ተቀላቀለች፡፡ በፖሊስ አባልነት የግድያ ወንጀል ምርመራዎችን በማጣራትም የአባቷ ገዳይ ላይ መድረስ ችላለች፡፡
ጎሜዝ የተባለው የአባቷ ገዳይ በ2013 በሌላ የነፍስ ማጥፋት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ 12 አመታትን ታስሮ እንደወጣ ካወቀች በኋላ የሚገኝበትን ቦታ አፈላልጋ በማወቅ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውል አድርገዋለች፡፡
ጂስሊየን ሲልቫ ዴዲውስ የአባቷ ገዳይ ወደ ሚገኝበት የእርሻ ስፍራ ከሄደች በኋላ የዛሬ 25 አመት በፈጸመው ወንጀል በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን እርሷም የሟቹ የጓደኛው አባት መሆኗን ነግራው ወደ እስር ቤት ይዛው ሄዳለች፡፡
እንስቷ የገዳዩን መያዝ በቁጥጥር ሰር ያዋለቸውም እርሷ እንደሆነች ለቤተሰቦቿ ስትነግራቸው የተሰማቸው ስሜት ሁሌም ከአዕምሮዋ እንደማይጠፋ ተናግራለች፡፡