ፎርብስ በዚህ አመት ስምንት ስፖርተኞች ከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማስገባት መቻላችውን ገልጿል
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከማንቸስተር ዩናይትድ ወደ ሳኡዲ አረቢያው ክለብ አልናስር ከተዛወረ በኋላ የአለማችን ከፍተኛው ተከፋይ ስፖርተኛ ሆኗል።
የ38 አመቱ ፖርቹጋላዊ ባለፉት 12 ወራት 138 ሚሊየን ዶላር ማግኘቱን የፎርብስ መረጃ ያሳያል።
የፒኤስጂ ተጫዋቾቹ አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ እና ፈረንሳዊው ኪሊያን ምባፔም ሮናልዶን በመከተል እስከ ሶስተኛ ያለውን ደሰጃ ይዘዋል።
በፎርብስ መረጃ መሰረት በዚህ አመት ስምንት ስፖርተኞች ከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማስገባት ችለዋል።