የዓለም ላጤዎች ብዛት 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን መድረሱ ተገልጿል
ዓለም አቀፉ የላጤዎች ቀን እንዴት አለፈ?
በየዓመቱ በፈረንጆቹ ህዳር 11 የሚከበረው የላጤዎች ቀን በመላው ዓለም የሚከበር ሲሆን ቻይነዎያን ላጤዎች በዓሉን በኩራት እንደሚያከብሩት ይገለጻል፡፡
በዓሉ በየዓመቱ ከቻይና በተጨማሪም በእስያ ፣አውሮፓ እና አሜሪካ በድምቀት የሚከበር ሲሆን የንግድ ኩባንያዎች በጉጉት እና በተለያዩ ዝግጅቶች የሚጠብቁት በዓለም ነው፡፡
ከፈረንጆቹ 1993 ጀምሮ አየደመቀ እና ትኩረት እየሳበ የመጣው ይህ በዓል በሸመታ፣ ወደ አደባባዮች በመውጣት ትውውቅ በመፍጠር፣ ጋብቻ በመፈጸም እና የተለያዩ ግብይቶችን በመፈጸምም በየሀገራቱ ይከበራል፡፡
የቻይና ሳይንቲስቶች የተራራቁ ፍቅረኛሞች መሳሳም የሚያስችል ማሽን መስራታቸውን ገለጹ
በተለያዩ የፌሽታ ፕሮግራሞች የሚከበረው ይህ በዓል በአንድ ቀን ብቻ ከ150 ቢሊዮን ዶላር በላይ ግብይት የሚፈጸምበት ዓለም አቀፍ በዓል ነው፡፡
በዓለማችን አሁን ላይ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ላጤዎች እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን የኑሮ ውድነት፣ የስራ ጫና ፣ የግል ህይወት ምርጫ እና የጾታ አለመመጣጠን ለላጤዎች ቁጥር መብዛት ዋነኞቹ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል፡፡
አውሮፓ እና እስያ ከፍተኛ የላጤዎች ቁጥር ያለባቸው አህጉራት ሲሆኑ በሀገር ደረጃ ደግሞ ኖርዌይ፣ፊንላንድ፣ዴንማርክ፣ ጀርመን ፣ኢስቶኒያ እና ጃፓን ደግሞ ከፍተኛ የላጤ ቁጥር ያለባቸው ሀገራት ናቸው፡፡
የኮሮና ቫይረስ መከሰት የላጤዎችን ቁጥር እንዲጨምር ካደረጉ ዓለም አቀፍ ክስተቶች መካከል አንዱ ሲሆን የማህበራዊ ትስስር ገጾች፣ የመጣበሻ መተግበሪያዎች፣ ትምህርት ቤቶች እና የስራ ቦታዎች ዋነኛ የፍቅር ግንኙነት መመስረቻ ስፍራዎች ናቸውም ተብሏል፡፡
እንደ ዓለም አቀፉ የመረጃ ተቋም ስታተስቲካ ጥናት ከሆነ ወንዶች ከሴቶች አንጻር ለላጤነት የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡