አሰልጣኙ ኳስን መሰረት አድርገው መጫወት ከሚመርጡ አሰልጣኞች መካከል የሚጠቀስ ነው
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ሆነ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አሰልጣኝ ውበቱ አባተን የብሔራዊ ቡድኑ (የዋልያዎቹ) ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መምረጡ ተገለጸ።
አሰልጠኝ ውበቱ በሀገር ውስጥ የተለያዩ ክለቦችን ያሰለጠነ ሲሆን በሱዳን አል-አሕሊ ሸንዲን አሰልጥኗል፡፡
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ2003 ዓ.ም የውድድር ዘመን ኢትዮጵያ ቡናን እየመራ የሊጉ አሰልጣኝ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ለበርካታ ዓመታት በተለያዩ አሰልጣኞች ያላሳካውን የፕሪሚየር ሊግ ድል በአልጣኝ ውበቱ አማካኝነት በማሳካቱ በክለቡ ውስጥ ተጠቃሽ ውጤታማ አሰልጣኝ ሆኗል፡፡
ከኢትዮጵያ ቡና በተጨማሪ ከዚህ ቀደም የአዳማ ከነማ ፣ የሀዋሳ ከነማ እና የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ የነበረው ውበቱ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በተቋረጠው በዚህ የውድድር ዓመት ሰበታ ከተማን በ17 ጨዋታዎች መርቷል፡፡
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ኳስን መሰረት አድርገው መጫወትን ከሚመርጡ አሰልጣኞች መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ የነበረው ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ውሉ ቢጠናቀቅም በድጋሚ ያልተመረጠበትና አዲስ አሰልጣኝ እንዲመረጥ የተወሰነበት ምክንያት ይፋ አልተደረገም፡፡