ከአውሮፓ ህዝብ ውስጥ 17 በመቶዎቹ ለድህነት ሊጋለጡ እንደሚችል ተገልጿል
ወጣት አውሮፓዊያን ወደ ድህነት የመውረድ ስጋት ውስጥ መግባታቸው ተገለጸ፡፡
የዓለማችን ሀብታሙ አህጉር አውሮፓ ሲሆን ላለፉት ዓመታት በተለያዩ ምክንያች ብዙ ችግሮችን በማስተናገድ ላይ የገኛል፡፡
ለተቀረው ዓለም የሰብዓዊ እና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ የሚታወቀው አውሮፓ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ዳግም ጦርነት በማስተናገድ ላይ ይገኛል፡፡
ሩሲያ ወደ ዩክሬን ጦሯን መላኳን ተከትሎ የተጀመረው ይህ የአውሮፓ ጦርነት የአካባቢውን ሀገራት ስጋት ላይ ጥሏል፡፡
የአውሮፓ ስታት የተሰኘው ተቋማ ባወጣው ጥናት መሰረት 20 በመቶ የአህጉሪቱ ወጣቶች ወደ ድህነት ሊወርዱ ይችላሉ፡፡
እንደ ተቋሙ ጥናታዊ መረጃ ከሆነ እድሜያቸው ከ15 እስከ 29 ዓመት ድረስ ያሉ ወጣቶች ከሌላው ማህበረሰብ የበለጠ ወደ ድህነት የመግባት ስጋት አይሎባቸዋል፡፡
ወደ ድህነት ይወርዳል የተባለው የአውሮፓ ህዝብ ውስጥም 17 በመቶ ድርሻ ያላቸው ሲሆን ተከታታይ ማሻሻያዎች ካልተደረጉ ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ተገልጿል፡፡
ላቲቫ፣ ማልታ፣ ኢስቶኒያ ፣ክሮሺያ ፣ዴንማርክ እና ስዊድን ከሌላው ማህበረሰብ ለየት ባለ መንገድ ወጣቶች የበለጠ ለድህነት የተጋለጡ ሲሆን በዘጠን የአውሮፓ ሀገራት ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ መረጃ መገኘቱን ጥናቱን ዋቢ አድርጎ ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡