ልዩልዩ
ናይጄርያዊቷ የ102 ዓመት አዛውንት ቀጣይ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ለመሆን ፍላጎት አለኝ አሉ
ፕሬዝዳንትን ሞሃመዱ ቡሃሪ የስልጣን ቆይታቸው በማገባደድ ላይ መሆናቸው ይታወቃል
አዛውንቷ ኢዜአንያቼ በበርካታ ናይጀርያዊያን ዘንዳ ‘ማማ አፍሪካ’ በመባል ይታወቃሉ
ናይጀርያዊቷ የ102 ዓመት አዛውንት በ2023 የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ለመሆን ፍላጎት እንዳለቸው ገለጹ።
በበርካታ ናይጄርያዊያን ዘንደ ‘ማማ አፍሪካ’ በመባል የሚታወቁት ናይጀርያዊቷ አዛውንት ኖንዬ ጆሴፊን ኢዜአንያቼ ኤንቲኤ ለተባለው ቴሌቭዥን እንዳሉት ከሆነ “የናይጀርያው አዲሱ ትውልድ ፈቃደኛ ከሆነ ፕሬዝዳንት የመሆን ፍላጎት አለኝ” ብለዋል።
ከአግዋታ፣ አናምብራ ግዛት የተገኙት ኢዜአንያቼ ለዘመናት ‘‘ቮይስ ፎር ሲንየር ሲትዝንስ ኦቭ ናይጄርያ’ እንደሆኑም ይነገርላቸዋል።
በናይጀርያ ለፕሬዝዳንትነት በሚወዳደሩ እጩ ፖለቲካኞች ዝቅተኛ እድሜ 35 ሲሆን ከፍተኛ ተብሎ የተቀመጠ የእድሜ ገደብ የለም።
አዛውንቷ ፕሬዝዳንት የመሆን ፍላጎት እንዳለቸው መግለጻቸውን ተከትሎ ስማቸው ከነ የኦል ፕሮግረሲቭ ኮነግረስ (ኤፒሲ) ፓርቲ ሊቀመንበር አህመድ ቲኒዩ፣ የኢቦኒ ግዛት ገዥ ዴቪድ ኡማሂ እና የሴኔቱ ዋና ኃለፊ ዊፕ ኦርጂ ኡዞር ካሉ ዝርዝር ተርታ እንደተካተተም ነው ተገልጿል።
የወቅቱ ፕሬዝዳንትን ሞሃመዱ ቡሃሪ ናይጀርያን ለሁለት የስልጣን ዘመናት በመምራት የስልጣን ቆይታቸው በማገባደድ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።