ከናይጀሪያ እስርቤት ያመለጡ ከ3ሺ በላይ እስረኞች እስካሁን አልተያዙም ተባለ
በናይጀሪያ 69ሺ በላይ እስረኞች ይገኛሉ
በናይጀሪያ ከባለፈው አመት ጀምሮ 4860 የሚሆኑ እስረኞች ከሀገሪቱ የእስረኛ ማቆያዎች አምልጠዋል
የናይጀሪያ መንግስት እንደገለጸው እስርቤት ሰብረው ያመለጡ ከ3ሺ በላይ እስረኞች እስካሁን አለመያዛቸውን ገለጸ፡፡
ከባለፈው አመት ጀምሮ 4860 የሚሆኑ እስረኞች በሀገሪቱ በነበረው የእስረኛ ማቆያ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ያመለጡ ሲሆን የተያዙት 984 የሚሆኑት ብቻ መሆናቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
የሀገር ውስጥ ሚኒስትር በሰጠው መግለጫ 3876 የሚሆኑ እስረኞች አልተያዙም፡፡
እስረኞቹን ተከታትሎ ለመያዝ፣የሁሉንም እስረኞች ባዮሜትሪክስ መውሰዱን የገለጹት ሚኒስትሩ ይህ እስረኞቹን ለመያዝ ተስፋ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
በናይጀሪያ በቅርቡ ፖሊስ ጣቢያዎችንና እስርቤቶችን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ተከታታይ ጥቃቶች ሲከፈቱ ቆይተዋል፡፡ በፈረንጆቹ ጥቅምት 22፣ፍርድ ሲጠባበቁ የነበሩ 837 እስረኞች በደቡብ ምእራብ ናይጀሪያ ከሚገኝ እስርቤት ማምለጣቸው ተነግሯል፡፡
በናይጀሪያ 69ሺ በላይ እስረኞች የሚገኙ ሲሆን 50ሺ የሚሆኑት ፍርድ በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡