ፖለቲካ
የቀድሞው የሌጎስ ገዢ ለናይጀሪያ ፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደሩ ገለጹ
የ69 ዓመቱ ቦላ ቲንቡ የናይጀሪያ ፕሬዘዳንት መሆን የህይወት ዘመን አቅዴ ነው ብለዋል
የቀድሞው የሌጎስ ገዢ ለናይጀሪያ ፕሬዘዳንትነት እንደሚወዳደሩ ገለጹ
የቀድሞው የሌጎስ ገዢ ለናይጀሪያ ፕሬዘዳንትነት እንደሚወዳደሩ ገለጹ፡፡
ናይጀሪያ በሚቀጥለው ዓመት ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የምታካሂድ ሲሆን አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዘዳንት መሀመዶ ቡሃሪ በምርጫው አይወዳደሩም ፡፡
ፕሬዘዳንት ቡሃሪ በምርጫው ላይ የማይወዳደሩት አገሪቱ ህገ መንግስት አንድ ፕሬዘዳንት ከሁለት ጊዜ በላይ በስልጣን ላይ እንዳይቆይ ስለሚከለክል ነው፡፡
የቀድሞው የሌጎስ ገዢ ቦላ ቲንቡ በሚቀጥለው ዓመት ለሚካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ላይ እንደሚሳተፉ ተናግረዋል፡፡
የ69 ዓመቱ ቦላ ቲንቡ የናይጀሪያ ፕሬዘዳንት መሆን የህይወት ዘመን አቅዴ ነው ያሉ ሲሆን ኦል ፕሮግረሲቭ ፓርቲ ወይም ኤፒሲን ወክለው እንደሚወዳደሩ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ቦላ ቲንቡ በፕሬዘዳንት ውድድር ዙሪያ አሁን ላይ በስልጣን ላይ ካሉት ሙሃመዶ ቡሃሪ ጋር መምከራቸውን ዘገባው አክሏል፡፡
ይሁንና ቦላ ቲንቡ የጤናቸው ሁኔታ አስተማማኝ አለመሆኑ እና ከዚህ በፊት በሙስና ወንጀል መጠርጠራቸው የፕሬዘዳንት ውድድራቸውን ሊያደናቅፈው እንደሚችል ተገልጿል፡፡