“ለመማር አሁን ቢሆን አልረፈደም”- የ50 ዓመቷ ናይጀሪያዊት ተማሪ
የ50 ዓመቷ ሻዴ አጃይ “ይህንን ዩኒፎርም በመልበሴ ህፍረት አይሰማኝም”ም ስትልም ተናግራለች
አጃይ በእድሜዋ ለሚሳለቁባትም “የፈለጋችሁትን በሉ መማሬን እቀጥላለሁ” ስትል ምለሽ ሰጥታለች
ሻዴ አጃይ እስከ ጎልማሳነት እድሜዋ ትምህርት ቤት የመርገጥ እድል ያላጋጠማት ናይጀርያዊት ናት፡፡ ይሁን እንጅ አሁን ላይ የ50 ዓመት ጎልማሳዋ ሻዴ፤ በእድሜ አራት እጥፍ ከምትበልጣቸው ልጆች ጋር በደስታ በመማር ላይ ናት፡፡
የሐምራዊ ቀሚስ ዩኒፎርሟን በመልበስም በናይጄሪያ ምዕራባዊ ኩራ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ኢሎሪን ውስጥ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ተማሪዎችን ተቀላቅላ እውቀትን እየገበየች ነው ይለናል የሮይተርስ ዘገባ፡፡
“ይህንን ዩኒፎርም በመልበሴ ህፍረት አይሰማኝም”የምትለው ሻዴ አጃይ በልጅነቷ ትምህርት ከመከታተል ይልቅ በአክስቷ ሱቅ ውስጥ ስተሰራ ማሳለፏንና አሁን የኪስ ቦርሳዎችን እና ሻንጣዎችን በመስራትና እና በመሸጥ ንግድ ላይ ተሰማርታ የራሷን ህይወት በመምራት ላይ መሆኗ ተናግራለች:: አጃይ በንግድ ቢሳካለትም ግን ማንበብ ወይም መፃፍ አለመቻሏ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ወደኋላ እንደጎተተት ታምናለች ፡፡
አጃይ ባለፈው ዓመት ትምህርቷን ለመከታተል ተመዝግባ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ሳትማር የቆየች ቢሆንም፤ ትምህርት ቤቶች በጥር ወር መከፈታቸውን ተከትሎ የመማር እድል አግኝታ መማር ጀምራለች፡፡
ዕድሜያቸው ከ 11 እስከ 13 ዓመት በሆኑ ተማሪዎች በተከበበ የእንጨት ጠረጴዛ ላይ ቁጭ ብላ ለጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እጇን በትህትና በማንሳት በክፍል ውስጥ ትሳተፋለችም ይላል ዘገባው፡፡
የአጃይ አስተማሪ ናስራት ቡሳሪ፤ የእድሜ ልዩነት ቢኖርም አጃይ ምንም የመደናገጥ ምልክት እንደማይታይባት ነው የሚገልፁት፡፡ “ራሷን ከነሱ ጋር በማላመድ፣ አብራ በመጫወት፣በማውራትና በመወያየት ነው የምታሳልፈው” በማለት፡፡
ልጇ ሾላ አዴቦዬ በበኩሏ መጀመርያ ላይ ትምህርት ቤትን እና ሥራን ማመጣጠን እና መገለልን ለመቋቋም ከባድ እንደነበር አስታውሳ፤ እናቷ ከልጆች ጋር በመሆን ትምህርት ቤት መግባቷን እንዳሳፈራትና በኋላ ግን ነገሮች መለመዳቸውን ተናግራለች፡፡
“ሁሌ የመማር ፍላጎት ነበራት፤ይሁን እንጅ እስካሁን መማር አልቻለችም ነበር” በማለትም የእናቷን የመማር ጥማት ከፍተኛ እንደነበር አዴቦዬ ገልፃለች፡፡
አሁንም ቢሆን ከትምህርት መልስ ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ሻንጣዎችን እምደምትሰራና ለደንበኞቿ እንደምተቀርብ የገለጸቸው አጃይ ለሚቀጥሉት አራት አመታት በትምህርቷ እንደምትቀጥልም አስታውቃለች፡፡
ለምትሰራው ስራ ትምህርት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው የሚል ፅኑ እምነት ያላት አጃይ “በአከባቢዮ ያሉ ሰዎች ማንብብና መጻፍ በመቻላቸው በቢዝነሳቸው ስኬታማ ናቸው” ስትልም ነው ለትምህርት ያላት ፍቅር የገለጸቸው፡፡
በዚህ እድሜ መማሯ ግርምት ፈጥሮባቸው ለሚቀልዱባት ሰዎችም “ለእንደዚህ አይነት ሰዎች ጀሮ አለመስጠት የኔ ግዴታ ነው፤ እናም የፈለጉተን ቢሉ መማሬን እቀጥላለሁኝ” ብላለች የ50 ዓመት ናይጀርያዊቷ ተማሪ ሻዴ አጃይ፡፡