የአፍሪካ 20 ቢሊየነሮች ጠቅላላ ሀብት 82 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር እንደሚደርስ ፎርብስ አስታውቋል
በፎርብስ የ2024 የቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ አፍሪካ 20 ባለጠጎቿን አስመዝግባለች።
የቢሊየነሮቹ ሃብት በ2023 ከነበረበት በ900 ሚሊየን ዶላር ጨምሮ 82 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር እንደሚደርስም ተገምቷል።
በዚህ የፈረንጆቹ አመት የቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ ደቡብ አፍሪካ ስድስት፣ ግብጽ አምስት እንዲሁም ናይጀሪያ አራት ቢሊየነሮቻቸውን አስመዝግበዋል።
በቢሊየነሮቹ ዝርዝር ውስጥ ሞሮኮ ሁለት፣ አልጀሪያ፣ ታንዛኒያ እና ዚምባቡዌ ደግሞ አንድ ማስመዝገባቸውንም የፎርብስ መረጃ ያሳያል።
ሀብታቸው በ400 ሚሊየን ዶላር አድጎ 13 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር የደረሰው ናይጀሪያዊው አሊኮ ዳንጎቴ የአህጉሪቱ ቁጥር 1 ባለጠጋ ሆነዋል።
የ91 አመቱ ሞሮኳዊ ኦታማን ቤንጀሉን ደግሞ በ2024 የአፍሪካ አዛውንት ቢሊየነሮች ዝርዝርን በቀዳሚነት ይመራሉ። በአለማቀፍ ደረጃ ደግሞ 2050ኛ ደረጃን ይዘዋል።
አምስት የደቡብ አፍሪካ ዜግነት ያላቸው ቢሊየነሮች በፎርብስ እድሜ ጠገብ የአፍሪካ ቢሊየነሮች ደረጃ ተካተዋል።
የፎርብስ 10 የአፍሪካ አዛውንት ቢሊየነሮችና የሀብት መጠናቸውን ይመልከቱ፦