በ2023 በሞት ይህችን ዓለም የተሰባቱ ቢሊየነሮች እነማን ናቸው?
የጣሊያን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ ቤርሎስኮኒን ጨምሮ 21 ቢሊየነሮች በ2023 ህይወታቸው አልፏል

በፎርብስ መረጃ መሰረት በአለማችን 2 ሺህ 640 ቢሊየነሮች አሉ
በተጠናቀቀው 2023 አለማችን በርካታ ቢሊየነሮችን በሞት አጥታለች።
አሜሪካዊው አቀንቃኝ ጂሚ ቡፌት እና የጣሊያን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ ቤርሎስኮኒን ጨምሮ 21 ቢሊየነሮች ህይወታቸው አልፏል።
በዚህ አመት ህይወታቸው ካለፈው ቢሊየነሮች ውስጥ አስራ አንዱ አሜሪካውያን ሲሆኑ ሶስት ህንዳውያን እና ሁለት ማሌዥያውያን ይገኙበታል።
የሟቾቹ ቢሊየነሮች አማካይ እድሜ 85 ሲሆን፥ ግማሾቹ ከ90 አመት በላይ ናቸው።
ቀለም ቢሊየነር ያደረጋቸው ህንዳዊው አሽዊን ዳኒ በ2023 ህይወታቸው ካለፈው ቢሊየነሮች በሀብት መጠናቸው ቀዳሚ ናቸው ተብሏል። የዳኒ ሃብት 8 ቢሊየን ዶላር እንደሚደርስ የፎርብስ መረጃ ያሳያል።
ሲልቪዮ ቤርሎስኮኒ በ6 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር፣ የአይቴል መስራቹ ጎርደን ሞር በ6 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር፣ የሪል ስቴት ከበርቴው ሳም ዚል በ5 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ይከተላሉ።
በ2023 ህይወታቸው ያለፈ ቢሊየነሮች የሃብት መጠንና እድሜያቸው ቀጥሎ ቀርቧል፦
1. ሞሃመድ አል ፋያድ
ዜግነት - ግብጻዊ
ሃብት - 2 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 94
2. ሲልቪዮ ቤልሮልስኮኒ
ዜግነት - ጣሊያናዊ
ሃብት - 6 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 86
3. ጂሚ ቡፌት
ዜግነት - አሜሪካዊ
ሃብት - 1 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 76
4. ቼን ሊፕ ኪዮንግ
ዜግነት - ማሌዥያዊ
ሃብት - 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 76
5. አሽዊን ዳኒ
ዜግነት - ህንዳዊ
ሃብት - 8 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 80
6. ካርል ዴሳንቲስ
ዜግነት - አሜሪካዊ
ሃብት - 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 84
7. ታን ስሪ ዳቱክ ናናሊንጋም
ዜግነት - ማሌዥያ
ሃብት - 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 78
8. ማሳቶሺ ኢቶ
ዜግነት - ጃፓን
ሃብት - 4 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 96
9. ሚኪ ጃግቲያኒ
ዜግነት - ህንዳዊ
ሃብት - 5 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 71
10. ሸልደን ላቪን
ዜግነት - አሜሪካዊ
ሃብት - 3 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 90
11. ቶማስ ሊ
ዜግነት - አሜሪካዊ
ሃብት - 2 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 78
12. ቴድ ለርነር
ዜግነት - አሜሪካዊ
ሃብት - 6 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 97
13. ኬሹብ ማሂንድራ
ዜግነት - ህንዳዊ
ሃብት - 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 99
14. ክላይተን ማትሂሌ
ዜግነት - አሜሪካዊ
ሃብት - 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 82
15. ቢሊ ጆይ ማክኮምብስ
ዜግነት - አሜሪካዊ
ሃብት - 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 95
16. ጎርዶን ሞር
ዜግነት - አሜሪካዊ
ሃብት - 6 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 94
17. ቻርለስ ሙንገር
ዜግነት - አሜሪካዊ
ሃብት - 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 99
18. ሺ ዌን ሎንግ
ዜግነት - ታይዋን
ሃብት - 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 95
19. ታንግ ሺያኡ
ዜግነት - ቻይናዊ
ሃብት - 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 55
20. ሳም ዚል
ዜግነት - አሜሪካዊ
ሃብት - 5 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 81
21. ዣኦ ኒንግ
ዜግነት - አሜሪካዊ
ሃብት - 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር
እድሜ - 56