በኢትዮጵያ በህገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ ከ10 ሺ በላይ ስደተኞች መመዝገባቸውን ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ ገለጹ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅሬታ የሚነሳበት ይህ የአገልግሎት መስሪያ ቤት በርካታ ማሻሻያዎችን አድርጓል ብለዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከወራት በፊት ሶስት ከፍተኛ ኃላፊዎች ከኃላፊነት መነሳታቸው ይታወሳል
በኢትዮጵያ በህገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ ከ10 ሺ በላይ ስደተኞች መመዝገባቸውን ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ ገለጹ ።
የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የውጭ ስደተኞች እንዲመወገቡ ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት፣ በኢትዮጵያ በህወጥ መንገድ የሚኖሩ 10467 ስደተኞችን መመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስተር ዐበይ በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅሬታ የሚነሳበት ይህ የአገልግሎት መስሪያ ቤት በርካታ ማሻሻያዎችን አድርጓል ብለዋል።
መስሪያ ቤቱ ከፓስፖርት አሰጣጥ አገልግሎት ጋር በተገናኘ በርካታ ቅሬታ የሚቀርብቀት ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጥር 2015 ዓ.ም ሶስት ከፍተኛ ኃላፊዎች ከኃላፊነት መነሳታቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚንስትር ከኃላፊነት ያነሱት የአገልግሎቱን በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ የነበሩትን አቶ ብሩህተስፋ ሙልጌታን፣ በምክትል ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ የነበሩትን ፍራኦል ጣፋ እና ታምሩ ግንበቶንን ነው።
ይህን ተከትሎ ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ከሐምሌ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተቋሙን በዋና ዳይሬክተርነት እየመሩ ነው።
በቅርቡ የፌደራል ዋና ኦዲተር በህዝብ ተወካዮች ባቀረበው ሪፖርት የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት ያለአግባብ በግለሰቦች ስም በተከፈተ አካውንት 17 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን መግለጹ ይታወሳል።
"የተከማቹ ቅሬታዎች መቶ በመቶ ተፈተዋል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐበይ አገልግሎቱ በቀን ይሰጥ የነበረውን የፓስፖርት መጠን ከ900 ወደ 1700 ከፍ አድርጓል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት ከተመዘገቡት ህገ ወጥ ስደተኞች ውስጥ 18ሺ የሚሆኑት ቅጣት ከፍለዋል።
በኢ ቪዛ ጨምሮ በ88 ሀገራት የቪዛ አገልግሎት በመክፈት ለ819,278 ሰዎች የቪዛ አገልግሎት መሰጠቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል።
በቅርቡ ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ ገደብ ከሚጥለው ፍርድ ቤት በተጨማሪ ለኢምግሬሽን ሰራተኞች የሚሰጥ ረቂቅ አዋጅ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። ይህ ረቂቅ አዋጁ አስፈጻሚው አካል የፍርድ ቤቶችን ስልጣን እንዲሻማ ያደርገዋል የሚል ትችል ቀርቦበታል።