ትራምፕ ቻይናን መጎብኘት እንደሚፈልጉ ተገለጸ
ትራምፕ በዓለ ሲመታቸውን ከመፈጸማቸው ቀደም ብሎ ንብረትነቱ የቻይናው ባይትዳንስ የሆነው ቲክቶክ በአሜሪካ አገልግሎት መስጠቱን አቁሟል
ትራምፕ በዓለ ሲመታቸውን ከመፈጸማቸው ቀደም ብሎ ንብረትነቱ የቻይናው ባይትዳንስ የሆነው ቲክቶክ በአሜሪካ አገልግሎት መስጠቱን አቁሟል
ትራምፕ ቻይናን መጎብኘት እንደሚፈልጉ ተገለጸ።
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመታቸውን ፈጽመው ኃይትሀውስ ከገቡ በኋላ ቻይናን የመጎብኘት ፍላጎት እንዳላቸው ሮይተርስ የአሜሪካውን ዋል ስትሪት ጆርናል ጠቅሶ ዘግቧል።
በአሜሪካ አገልግሎቱን ያቆመው ቲክቶክ በአዲሱ የትራምፕ አስተዳደር የመመለስ ተስፋ እንዳለው ገለጸ
ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ዝግጁ የሆነችው ቻይና በነገው የትራምፕ በዓለ ሲመት ላይ የሚታደም በምክትል ፕሬዝደንት ሀን ዜንግ የሚመራ የልኡክ ቡድን እንደምትልክ ባለፈው አርብ እለት አስታውቃለች። ትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዝደንት በተወካዮቻቸው በኩል መጭው የአሜሪካ ፕሬዝደንት የቻይና መሪንዠ አሜሪካን እንዲጎበኙ መጋበዝን ጨምሮ በበርካታ አማራጮች ዙሪያ መምከራቸው ተዘግቧል።
ሮይተርስ አሜሪካ ካለው የቻይና ኢምባሲ በጉዳዩ ላይ መረጃ አለማግኘቱን ገልጿል።
ትራምፕ በዓለ ሲመታቸውን ከመፈጸማቸው ቀደም ብሎ ንብረትነቱ የቻይናው ባይትዳንስ የሆነው ቲክቶክ በአሜሪካ አገልግሎት መስጠቱን አቁሟል። ቲክቶክ አገልግሎቱን ያቆመው የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቲክ እንዲሸጥ ወይም አገልግሎት እንዲያቆም ያሳለፈው ውሳኔ በዛሬው እለት ተግባራዊ ከመሆኑ ቀደም ብሎ ትናንት ምሽት ነው።
አሜሪካ ቲክቶክ እንዲታገድ የወሰነችው ለቻይና መረጃ በመስጠት የብሔራዊ ደህንነት ስጋት እንደደቀነባት በመግለጽ ነበር።