የጥምቀት በዓልን ከኢትዮጵያ ጋር እያከበሩ የሚገኙ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
የጥምቀት በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ዕለት በማሰብ የሚከበር በዓል ነው

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሩሲያ እና ዮርዳኖስጥምቀትን በተመሳሳይ እለት ከሚያከብሩ ሀገራት መካከል ይገኙበታል
ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ዕለት በማሰብ የሚከበረው የጥምቀት በዓል በተለያዩ የአለም ሀገራት በሚገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ ዓመታዊ በዓሎች አንዱ ነው።
በዚህም ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ያሉ የእምነቱ ተከታዮች የጥምቀት በዓልን በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ለዘመናት እያከበሩ እዚህ ደርሰዋል።
በዓሉ ዛሬ ማለትም ጥቀምት 11 ከሚከበርባቸው ሀገራት ውስጥም ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ዮርዳኖስ ተጠቃሽ ናቸው።
የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ እና በኤርትራ በተመሳሳይ ኃይማኖታዊ ስርዓት ነው ተከብሮ የሚለውለው።
ከ90 ሚሊየን በላይ የኦርቶድክስ እምነት ተከታዮች ያሏት ሩሲያም የጥምቀት በዓልን በድምቀት በማክበር ላይ ትገኛለች።
የሩሲያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቅን እና ሶስቱ ስላሴዎችን ለማስታወስ በበረዶ ውሃ ውስጥ ራሳቸውን ሶስት ጊዜ ይነከራሉ።
የሩሲያ ኦርቶዶክሳዊያን ሶስት ጊዜ ራሳቸውን በበረዶ ውሃ ውስጥ መንከር ሀጢያታቸውን ያነፃል ብለው ያምናሉ።
የእምነቱ ተከታዮች በጥምቀት ወቅት ሁሉም ውሃ የተቀደሰ መሆኑን የሚያምኑ ሲሆን፥ በረዶውም ጤናቸው ላይ በጎ ተፅዕኖ እንዳለውም ያምናሉ።
ዩክሬን በሩሲያው ጦርነት ምክንያት የጥምቀት በዓልን የምታከብርበትን እለት በ2023 ቀይራ የጁሊያን የዘመን ቀመር ከሚከተሉ ሀገራት ጋር እያከበረች ነው።
ዩክሬናውያን ኦርቶዶክሶች እስከ 2023 ድረስ እንደ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በዛሬው እለት የኢየሱስ ክርስቶስን በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቅ በተለያዩ ስነስርአቶች ስታከብር ቆይታለች።
በተወሰኑ የአውሮፓ ሀገራት የሚገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችም በጥልቅ ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ በዋና ውድድር የታጀበን የጥምቀት በዓል ያከብራሉ።
በቦስኒያ እና ሄርዞጎቪኒያ የሚገኙት የእምነቱ ተከታዮች በቄሶች ወደ ውሃ የተጣለውን የእንጨት መስቀል ለመያዝ የሚደረግ የዋና ፉክክር ያደርጋሉ።
በዚህ የዋና ውድድር መስቀሉን መያዝ የቻለው እና ወደ መሬት የመለሰው ግለሰብ ዓመቱን በሙሉ የተባረከ ይሆናል ብለውም ያምናሉ።