የዘንድሮ ሀጅ በኮሮና ወረርሽኝ ምከንያት በተሳታፋዎች ቁጥር ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ ሙሉ በሙሉ ከተነሳ በኋላ የሚከበር ነው
11ዶቹ የሀጅ ስነስርአቶች
ስነስርአቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦
ኢኸራም በሜካ
ጠዋፍ አልቀዱም(ካባ መዞር)
በሳፉ እና ማረዋ መካከል የሚደረግ ጉዞ
በሚና የአንድ ቀን ታርዊያ
ጸሃይ ሲወጣ ወደ አረፋት ተራራ መሄድ
ሙዝዳልፋህ ላይ መቆም
በአቃባ ላይ ድንጋይ መወርመር
ዕርድ ማድረግና ጸጉር መላጨት
ጠዋፍአል-ኢፋዳ
ሶስቱን ጀመራት መወርወር
የስንብት ጠዋፍ
ኢድ አል አድሃ በእስልም እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩት ሁለት ዋና ባዓላት አንዱ ነው። ሌላኛው ትልቅ በዓል ደግሞ ኢድ አልፈጥር ነው።
የዘንድሮ ሀጅ በኮሮና ወረርሽኝ ምከንያት በተሳታፋዎች ቁጥር ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ ሙሉ በሙሉ ከተነሳ በኋላ የሚከበር ነው።
በዓለም ደረጃ የኮሮና ወረረሽኝ ተከስቶ የነበረበት ወቅች፣ በሀጅ ተጓዦች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ ይታወሳል።
በኮሮና ወቅት ሳኡዲ አረቢያ ትንሽ ቁጥር ያለው ምዕመን ተራርቆ እንዲያከብር የሚያስገድድ ህግም አውጥታ ነበር።
በዘንድሮ ሀጅ ለሀጅ ተጓዦች መመላሻ የሚሆን 1000 ባሶችን አዘጋጅታለች።
ለተጓዞች የአገልግሎች ክፍያ ቅናሽም ተደርጓል።በዘንድሮው ሀጅ 2.6 ሚሊዮን ህዝብ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።