የሟቾች ቁጥር 117 ደርሷል
በአፍሪካ የኮሮና ሟቾች ቁጥር 117 ደረሰ
በኮሮና ቫይረስ የሞቱ አፍሪካውያን ቁጥር 117 መድረሱን የአህጉሪቱ የበሽታዎች ቁጥጥር ማዕከል አስታውቋል፡፡ በ46 የአፍሪካ ሃገራት 3,924 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ያለው ማእከሉ 276 ሰዎች ማገገማቸውንም ገልጿል፡፡
288 ኬዞች ሪፖርት በተደረጉበት የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና 4 ሰዎች መሞታቸውንና 5 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውንም ማዕከሉ ይፋ አድርጓል፡፡
16 ሰዎች በቫይረሱ በተያዙባት ኢትዮጵያ እስካሁን የሞተ ሰው አለመኖሩ የሚታወቅ ነው፡፡