ኮሮና ቫይረስ እንደየሁኔታው በስልክዎት ላይ እስከ 9 ቀናት ሊቆይ ይችላል
የእጅ ስልክዎን አሁንኑ ያጽዱ
የተላላፊ በሽታዎች እና የኢሚዩኖሎጂ ስፔሻሊስቱ ከኮሮና ጋር በተያያዘ ለእጅና ለሌሎች ነገሮች ንጽህና የምንሰጠውን ትኩረት ያህል ለእጅ ስልኮቻችን መስጠት ያስፈልጋል ይላሉ፡፡
በእንግሊዝ ግሪፊት ዩኒቨርስቲ የተላላፊ በሽታዎች ፕሮፌሰሩ ኒጌል ማክሚለን ከሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ጋር አነጻጽረው ኮሮና በበብዙ ቦታዎች ላይ ሊኖር ቢችልም በቀን በአማካይ 2 ሺ 617 ጊዜ የምነናካቸውን እጅ ስልኮቻችንን ይበልጥ ልንጠነቀቅ ይገባል ሲሉ ይናገራሉ፡፡
ኮሮና ልስላሴ ባላቸው መስተዋቶች እና ፕላስቲኮች ላይ ረዘም ላሉ ቀናት ሊኖር እንደሚችልም ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡
ፕሮፌሰር ኒጌል እንደሚሉት በስማርት ስልኮቻቸን ላይ እንደየሁኔታው እስከ 9 ቀናት ድረስ ሊኖር ይችላል፡፡
“ኮሮና በየትኛውም ቦታ በተለይ እርጥበታማ በሆኑ ቦታዎች ላይ ዘለግ ላሉ ቀናት ሊቆይ ይችላል” ሲሉ ያስቀምጣሉ፡፡
ጥሩው ነገር እጅን እንደ ሌላ ተቀጥላ አካል መቁጠር ነው ይላሉ በእጅ ላይ ያለ ነገር ሁሉ ወደ ስልኩ እንደሚተላለፍ በመጠቆም፡፡
ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባትም ስልክዎን ከተጠቀሙ በኋላ ማጽዳት ይገባል፡፡
ስልክዎን በየትኛውም ቦታ አያስቀምጡ ሲጠቀሙ ከተጠቀሙም በኋላ ሌላም ሰው ከነካው ያጽዱት፡፡
ለማጽዳትም ሳኒታይዘር አለበለዚያም ለዚሁ ዓላማ በሚል የተዘጋጁ ለስላሳ የስክሪን/ሌንስ ማጽጃዎችን ይጠቀሙ፡፡
ነገር ግን ማጽጃዎቹ ከ60 እስከ 70 በመቶ አልኮል ሊኖረው ይገባዋል፡፡
ይህ ሁሉ ደግሞ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው እጅዎን የባለሙያዎችን ምክረሃሳብ በመከተል ሲያጸዱ እና ሲታጠቡ ብቻ ነው፡፡
ለ20 ሰከንዶች ያህል የአልኮል ይዘት ባላቸው መታጠቢያዎች በሳኒታይዘር አለበለዚያም በሳሙና መታጠቡ ቫይረሱን ለመከላከል እንደሚያስችልም ይነገራል፡፡