አቡዳቢ ነዳጅን ሳይጨምር ከወጪ ንግድ 190 ቢሊየን ድርሃም ገቢ ማግኘቷን አስታወቀች
ገቢው በፈረንጆቹ 2021 በ11 ወራ ውስጥ የተገኘ መሆኑን የአቡዳቢ ስታቲስቲክስ ማዕከል አስታውቋል
የውጭ ንግድ መጠኑ ከፈረንጆቹ 2020 ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር የ2 ነጥብ 9 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል
በፈረንጆቹ 2021 በ11 ወራት ብቻ በአቡ-ደቢ ወደቦች በኩል የተደረገ ነዳጅ-ነክ ያልሆነ የውጭ ንግድ መጠን 190 ቢልዮን ድርሃም እንደሚገመት ተገለጸ።
አቡ ዳቢ ስታቲስቲክስ ማዕከል መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ የውጭ ንግድ መጠኑ ካለፈው የፈረንጆቹ 2020 ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር የ2 ነጥብ 9 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል።
ከአጠቃላይ የውጭ ንግድ መጠኑ 83.63 ቢሊየን ዲርሃም የሚሆነው የገቢ ንግድ እንዲሁም 71.1 ቢሊዮን ድርሃም የወጪ ንግድ (ኤክስፖርት) የተደረገ እንደሆነም መረጃው ጠቁሟል።
አቡ ዳቢ ስታቲስቲክስ ማዕከል፡ ሳውዲ አረቢያ፣ ቻይና፣ አሜሪካ እና ኦማን የአቡ-ዳቢን ነዳጅ ነክ ያለሆነ የወጭ ንግድ ዋነኛ አጋሮች እንደሆኑም አመላክቷል።
ባለፉት 11 ወራት “ሳውዲ አረቢያ 4.87 ቢሊየን ድርሃም፣ ቻይና በ1.15 ቢሊየን ድርሃም፣ አሜሪካ በ1.46 ቢሊዮን ድርሃም እንዲሁም ኦማን በ1.144 ቢሊየን ድርሃም የሚገመት የውጭ ንግድ ልውውጥ አድርጓል”ም ብለዋል ማዕከሉ።
በአቡዳቢ ኢሚሬቶች በኩል የሚካሄደው ነዳጅ-ነክ ያልሆነ የሸቀጣሸቀጥ ንግድ በአቡዳቢ ኢሚሬቶች ምድር፣ ባህር እና አየር ወደቦች ብቻ በሚገቡ ወይም ከሱ በወጡ እቃዎች ላይ ብቻ የተገደበ ነው።