ዩኤኢ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ቀዳሚ የዓመቱ ኢንቨስትመንት መዳረሻ ተብላ ተመረጠች
ከዓለማችን ሀገራት ደግሞ ዘጠነኛዋ የኢንቨስትመንት ሀገር ሆናለች
ዩኤኢ በተጠናቀቀው 2021 ዓመት 20 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ስባለች
ዩኤኢ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ቀዳሚ የዓመቱ ኢንቨስትመንት መዳረሻ ተብላ ተመረጠች፡፡
ዓለም አቀፉ የሀገራት ዓመታዊ ኢንቨስትመንት ሪፖርት እንዳስታወቀው ዩኤኢ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ የኢንቨስትመንት መዳረሻ አገር ሆናለች፡፡
እንደዚህ ተቋም ሪፖርት ከሆነ ዩኤኢ ከዓለማችን ሀገራት መካከል ዘጠነኛዋ የኢንቨስትመንት ሳቢ ሀገር ሆና ተመርጣለች፡፡
የተባበሩት አረብ ኢምሬት በተጠናቀቀው 2021 ዓመት 20 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እንደሳበችም ተገልጿል፡፡
የዓለም ኢኮኖሚ በኮሮና ቫይረስ ክፉኛ በተመታበት በዚህ ወቅት ዩኤኢ ከፍተኛ መጠን ያለው የኢንቨስትመንት እድሎችን መፍጠር መቻሏንም ይህ ተቋም በዓመታዊ ሪፖርቱ አስታውቋል፡፡
ዩኤኢ በዓለማችን ካሉ ሰፊ መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችሉ ቀልጣፋ የአውሮፓላን ጣቢያዎች ካሏቸው ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ሀገር ስትሆን ኢምሬት አየር መንገድ እና ኢትሃድ አየር መንገድ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በዚህም ከዓረብ አገራ መካከል ቀዳሚ ከዓለማችን ደግሞ ዘጠነኛዋ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ሀገር ሆናለች ተብሏል፡፡ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ Aበዩኤኢ ገንዘባቸውን ያፈሰሱ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ቁጥር በ52 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
በአጠቃላይ በዩኤኢ 2ሺህ 577 ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ የተሳተፉ ሲሆን የ114 ሀገራት ዜግነት ያላቸው ሰዎችም በአገሯ በስራ ላይ ናቸው፡፡
ዩኤኢ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት 150 ቢሊዮን ዶላር ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ማቀዷንም ገልጻለች፡፡