በኮፕ28 ይፋ ለሆነው 'ክላሜት እና ሄልዝ ዲክላሬሽን' 2.7 ቢሊዮን ገንዘብ ተመደበ
ዲክላሬሽኑ የአለም መሪዎች በተገኙበት የአረብ ኢምሬትሱ የኮፕ28 ስብሰባ መጀመሪያ ላይ ነበር ይፋ የሆነው
189 ሚሊዮን የሚሆነው የአለም ህዝብ ለከባድ የአካባቢ የአየር ንብረት ክስተት ተጋላጭ ነው
በኮፕ28 ይፋ ለሆነው 'ክላሜት እና ሄልዝ ዲክላሬሽን' 2.7 ቢሊዮን ገንዘብ ተመደበ።
በኮፕ28 ይፋ ለሆነው 'የክላሜት እና ሄልዝ ዲክላሬሽን' የሚውል 2.7 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ መመደቡ ተገልጿል።
የኮፕ28 'የክላይሜት እና ሄልዝ ዲክላሬሽን' የአየር ንብረት ለውጥ በሚያስከትለው ችግር ምክንያት ሊመጣ የሚችለውን የጤና ችግር ለመከላከል የሚያስችል መርሃግብር ነው።
ዲክላሬሽኑ የአለም መሪዎች በተገኙበት የአረብ ኢምሬትሱ የኮፕ28 ስብሰባ መጀመሪያ ላይ ነበር ይፋ የሆነው።
132 ሀገራት የፈረሙበት ይህ ዲክላሬሽን ይፋ የሆነው 'የጤና ቀን' ይፋ ከመሆኑ ከአንድ ቀን በፊት ነው። መሪዎቹ ለመጀመሪያ ጊዜ የአየር ንብረት ለውጥን ተከትለው ከሚመጡት የሙቀት መጨመር፣ የአየር ብክለት እና በሽታዎች ማህበረቡ መጠበቅ እንዳለበት ተግባብተዋል።
ዲክላሬሽኑ ከብራዚል፣ ከፈረንሳይ፣ ከማላዊ፣ ከዩኬ እና ከአሜሪካ እና ከሌሎች ሀገራት ድጋፍ አግኝቷል።
189 ሚሊዮን የሚሆነው የአለም ህዝብ ለከባድ የአካባቢ የአየር ንብረት ክስተት ተጋላጭ ነው።