ኮፕ28 ጉባኤ በዱባይ ሲካሄድ ሰባተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል
የሆላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የኮፕ28 ጉባኤን ስኬት አደነቁ፡፡
በአረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ሰባተኛ ቀኑን ይዟል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር በመምከር ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ የተሳተፉት የሆላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሲግሪድ ካግ ለአልዐይን እንዳሉት ኮፕ28 የዓየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ስኬታማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የጉባኤው ዋነኛ ስኬት የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ መቋቋም ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯ ዓለም ለሚኖርባት ምድር የተሸለ ሀላፊነት እንዲወስድ ያደረገ ጉባኤ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯ አክለውም ሁላችንም በተናጥል የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከልን የምንወስደው እርምጃ ውጤት አያመጣም በዱባዩ የኮፕ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የጋራ ሀላፊነት አንድንወስድ የሚያደርግ የአየር ንብረት ፈንድ መቋቋሙ ጥሩ እርምጃ ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይ በሚደረገው ተመሳሳይ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ብዙ የተግባር ስራዎችን ሰርተን መሆን አለበት ሲሉም ካግ ተናግረዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተሯ ሀገራቸው ሆላንድም ለአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ 15 ሚሊዮን ዶላር እንደምታዋጣም ጠቅሰዋል፡፡
አይኤምኤፍ 11 የአየር ንብረት ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን ገለጸ
የጉባኤው አዘጋጅ የሆነችው አረብ ኢምሬት አመራር ጉባኤው ታሪካዊ እና ምድራችንን ከከፋ ጉዳቶች ሊጠብቁ የሚችሉ አዳዲስ ውሳኔዎች እንዲወሰን ማድረጉንም ጋግ ገልጸዋል፡፡
በርካታ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ማካካሻ ፈንድ ገንዘብ በማዋጣት ላይ ሲሆኑ ይህ ፈንድ በዓመት 100 ቢሊዮን ዶላር ከሀገራት እና ተቋማት ለመሰብሰብ እና የተጎዱ ሀገራትን እንደሚክስ ይጠበቃል፡፡
አረብ ኢምሬት ለዚህ ፈንድ 100 ሚሊዮን ዶላር ስታዋጣ፣ አሜሪካ 17.5 ሚሊዮን ዶላር፣ ብሪታንያ 40 ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ፣ ጃፓን 10 ሚሊዮን ዶላር፣ የአውሮፓ ህብረት ደግሞ 145 ሚሊዮን ዩሮ በድምሩ ለፈንዱ በሁለት ቀናት ውስጥ 400 ሚሊዮን ዶላር መዋጣቱ ተገልጿል።