አፍሪካ ለአየር ንብረት ጉዳት ማካካሻ 87 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ተገለጸ
አህጉሪቱ ከበለጸጉ ሀገራት በሚለቀቁ በካይ ጋዝ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳቶችን በማስተናገድ ላይ ትገኛለች
አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳትን ለመቀነስ በአጠቃላይ 3 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ተገልጿል
አፍሪካ ለአየር ንብረት ጉዳት ማካካሻ 87 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ተገለጸ፡፡
በአረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ስምንተኛ ቀኑን ይዟል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር በመምከር ላይ ይገኛል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ የአካባቢ ጥበቃ ቢሮ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶክተር ሊኑስ ሙፎር ለኢምሬት ዜና አገልግሎት እንዳሉት አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ሶት ትሪሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ገልጸዋል፡፡
የበለጸጉ ሀገራት ከኢንዱስትሪዎቻቸው በሚለቀቁ በካይ ጋዝ አማካኝነት አፍሪካ ብዙ ዋጋ እየከፈለች ነው ያሉት ዶክተር ሊኑስ በየዓመቱም አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም 87 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታልም ብለዋል፡፡
ቦይንግ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን የአፍሪካ ዳይሬክተር አድርጎ ሾመ
ይሁንና አሁን ላይ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በዓመት እያገኘች ያለው 30 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነውም ተበሏል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት በየዓመቱ እየጨመረ መሆኑን የሚናገሩት ዶክተር ሊኑስ የአፍሪካ ድርሻ 4 በመቶ ብቻ ነው ያሉ ሲሆን በአየር ንብረት ለውጥ ምክንት ከአመታዊ ምርቷ ላይ የ5 በመቶ ቅናሽ እንዲመዘገበ ማድረጉም ተገልጿል፡፡
በኮፕ28 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የአየር ንብረት ፈንድ መቋቋሙ ለአፍሪካ እና ለተቀረው ዓለም ስኬት እንደሆነም ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡
በዓለም ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከማያገኙ 733 ሚሊዮን ዜጎች ውስጥ 80 በመቶዎቹ አፍሪካዊያን ሲሆኑ የአየር ንብረት ለውጥ ፈንዱ ብዙ ዜጎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋልም ተብሏል፡፡
በኮፕ28 ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙ ከ200 በላይ ሀገራት መሪዎች እና ባለሙያዎች መካከል 117 ሀገራት በ2030 የታዳሽ ሀይል አቅርቦቶቻቸውን እንደሚያሻሽሉ ተናግረዋል፡፡
70 መንፈግስታት እና 39 ተቋማትም የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በጋራ ለመስራት ስምምነቶችን የተፈራረሙ ሲሆን ለአደጋ ተጋላጭ ሀገራትን እንደሚደግፉም ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡