ሀሎዊን የተሰኘው የእጅ ሰዓት የዓለማችን ውዱ ሰዓት ተብሏል
እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆቹ 2022 ዓመት ከዚህ በፊት ከነበረው በተለይም ለፋሺን ኢንዱስትሪው ጥሩ የሚባል እንደነበር ይጠቀሳል።
የእጅ ሰዓት ከፋሺን አልባሳት ወይም ጌጣጌጥ መካከል አንዱ ሲሆን በ2022 ዓመት ምርጥ እና ውድ የእጅ ሰዓት አይነቶች ይፋ ሆነዋል።
ሀሎዊን የእጅ ሰዓት
55 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣው ውዱ እና ቅንጡ የእጅ ሰዓት ሀሎዊን የእጅ ሰዓት የሚባል ሲሆን መስተዋቱ ከአልማዝ የተሰራ ነው ተብሏል።
ይህ ሰዓት ከሰዓትነት ይልቅ ወደ ጌጣጌጥነት ያደላል የተባለ ሲሆን 110 ካራት አልማዝ ወይም ዳይመንድ አለው።
ግራፍ ዳይመንድ
ግራፍ ዳይመንድ የተሰኘው ሌላኛው የእጅ ሰዓት የዓለሜችን ሁለተኛው ውዱ ሰዓት ሲባል የ40 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ተመን ወጥቶለታል።
ብሪገት ማሪ አንቶኔት
ብሪገት ማሪ አንቶኔት የተሰኘው ሌላኛው የእጅ ሰዓት ደግሞ የዓለማችን ሶስተኛው ውድ የእጅ ሰዓት ተብሏል።
በ30 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ እየተሸጠ ያለው ይህ የእጅ ሰዓት በፈረንሳቷ ንግስት ብሪገት አንቶኔት ስም የተሰራ ነው።
በምዕራባዊያን ዘመን አቆጣጠር 1782 ህይወታቸው እንዳለፈ የሚነገርላቸው ንግስቲቱ ሰዓቱን ሳይቀበሉት ህይወታችው ማለፉ ተገልጿል።
ቾፓድ የእጅ ሰዓት
ሌላኛው የ2022 ዓመት አራተኛው ውድ ሰዓት ቾፓድ የእጅ ሰዓት የሚሰኝ ሲሆን 25 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ አለው።
ፓቴክ ፊሊፕ
አምስተኛው የዓለማችን ውዱ የእጅ ሰዓት ፓቴክ ፊሊፕ ሄነሪ የሚሰኝ ሲሆን የሴቶች ሰዓት እንደሆነ ተገልጿል።
24 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል የተባለው ይህ የእጅ ሰዓት ለመስራት ስምንት ዓመታትን ፈጅቷል ተብሏል።
ጃኮብ የእጅ ሰዓት
ጃኮብ የተሰኘው የእጅ ሰዓት ደግሞ በስድስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ የ18 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ተለጥፎበታል።
ከፈረንጆቹ 1968 ዓመት ጀምሮ በመሰራት ላይ ያለው ሮሌክስ የተሰኘው የእጅ ሰዓት በ17 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ የዓለማችን ሰባተኛው ውድ የእጅ ሰዓት ተብሏል።