በ2022 የዓለማችን ምርጥ አየር መንገድ ተብለው የተሰየሙት የትኞቹ ናቸው?
ስካይትራክስ ከ14 ሚሊየን ደንብኞች ላይ መረጃ በማሰባሰብ አየር መንገዶችን ደረጃ ይፋ አድርጓል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 11 ደረጃዎችን በማሻሻል ከዓለም ምርጥ 100 አየር መንገዶች 26ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል
መቀመጨውን ብሪታኒያ ያደረገው ስካይትራክስ ኩባያ የ2022 የዓልም ምርጥ 100 አየር መንገዶችን ደረጃ ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል።
ኩብንያው ደረጃውን የሰጠው በ100 ሀገራት ከሚገኙ 14 ሚሊየን የአየር መንገዶች ደንበኞች ላይ መረጃን በማሰባሰብ እንደሆነ አስታውቋል።
በስካይ ትራክስ መረጃ መስረት በደንብኞች ምርጫ ከ1 እስከ 10ኛ ደረጃ የተቀመጡ አየር መንገዶችም፤
1 ኳታር አየር መንገድ
2 ሲንጋፖር አየር መንገድ
3 ኢሚሬትስ አየር መንገድ
4 ኦል ኒፖን አየር መንገድ
5 ጃፓን አየር መንገድ
6 ካንታስ አየር መንገድ
7 ቱርኪሽ አየር መንገድ
8 ኤር ፍራነስ አየር መንገድ
9 ኮሪያን ኤር አየር መንገድ
10 ስዊስ ኢነተርናሽናል አየር መንገዶች ናቸው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2022 የስካይትራክስ ደረጃ ከዚህ ቀደም ከነበረው 11 ደረጃዎችን በማሻሻል ከዓለም ምርጥ 100 አየር መንገዶች 26ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ ታውቋል።
በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2022 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ፣ የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ደረጃ አየር መንገድ፣ የአፍሪካ ምርጥ ኢኮኖሚ አየር መንገድ እንዲሁም በአፍሪካ ውስጥ ምርጥ የቢዝነስ ክላስ ምግብ አቅራቢነት ሽልማቶችን ማሸነፍ መቻሉ ተነግሯል።