በ2022 ምርጥ የካሜራ ጥራት አላቸው ተብለው የተመረጡ ስማርት ስልኮች የትኞቹ ናቸው…ʔ
ስማርት ስልኮችን ተመራጭ ከሚያደርጋው ውስጥ የካሜራ ጥራት አንዱ ነው
የስማርት ስልክ አምራቾች ለካሜራ ጥራት ትኩረት ሰጥው እየሰሩ ይገኛሉ
ስማርት ስልክ ግዢ ላይ የማሻሻጫ ነጥብ እየሆነ ከመጣው ውስጥ የካሜራ ጥራት ደረጃ አንዱ እየሆነ ይገኛል።
ከዋነኞች የስማርት ስልክ አምራቾች አፕል እና ሳምሰንግ ጀምሮ እስክ ጎግል እንዲሁም ሌሎችም የስማርት ስልኮች አሁን አሁን ካሜራዎቻው በሚያነሷቸው ከፍተኛ ጥራት ያለው ምስል ተመራጭ እየሆኑ መጥተዋል።
አፕል፣ ጎግል እና ሳሰንግን ጨምሮ ሁሉመወ የስማርት ስልክ አምራቾች የካራዎቻውን ጥራት ለመሳደግ አርቲፊሻል እንተለጀንስ ቴክኖሎጂን እስከመጠቀም ደርሰዋል።
በ2022 ባላቸው የካሜራ ጥራት ቀዳሚውን ስፍራ የያዙ ስማርት ስልኮች
አይፎን 14 ፕሮ
በቅርቡ ይፋ የተደረገው አይፎን 14 ፕሮ 48 ሜጋ ፒከስል ካሜራ የተገጠመለት ሲሆን፤ እጅግ ጥራት ያላቸው ምስሎችን ውብ፣ ተፈጥሯዊ ቀለሞች በጠበቀ መልኩ ማሳት ይችላል።
ሰፊ ማዕዘን ያለው ሌንሱ ምርጥ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ሲሆን፤ አነስተኛ ብርሃን ሲኖር እና በምሽት ጥራት ያላቸው ምስሎችን ያነሳል።
ጎግል ፒክስል 7 ፕሮ
ጎግል ፒክስል 7 ፕሮ ስማርት ፎን ሶስት ሌንስ ያለው ካራ የተገጠመለት ሲሆን፤ የካሜራው ጥራም 50 ሜጋ ፒክሰል መሆኑ ተጠቅሷል።
ስማርት ስልኩ ሲሆን፤ እጅግ ጥራት ያላቸው ምስሎችን ያነሳል የተባለ ሲሆን፤ 5 እጥፍ ዙም ያለው ሲሆን፤ ይህም በርቀት ላይ ያለ ነገርን በጥራት ለማንሳት ያስችለዋል።
ሳምሰንግ ጋላክሲ 22 አልትራ
ሳምሰንግ ጋላክሲ 22 አልትራ 40 ሜካ ፒከስል የካሜራ ጥራት ያለው ሲሆን፤ እስከ 8K ቪዲዮ ጥራት ድረስ መቅረጽ እንደሚችል ተነግሯል።
10 እጥፍ ዙም ያለው ሌንስ ያለው ሲሆን፤ ይህም በርቀት ላይ ያለ ነገርን በጥራት ለማንሳት ያስችለዋል።
ሶኒ ኤክስፒሪያ ፕሮ-1
ሶኒ ኤክስፒሪያ ፐሮ-1 እያንዳንዳቸው 12 ሜጋ ፒክስል የመስል ጥራት የሚያነሱ ሶስት ሌንሶች የተገጠሙለት ሲሆን፤ ይህ ምስለሎችን በጥራት እንዲያነሳ አስችሎታል ተብሎለታል።
ሁዋዌይ ሜት 50
በየትኛውም የዓለም ክፍል በሳተላይት የሚሰራ ሜት 50 ስማርት ስልክ ከጀርባው 4 የካሜራ ሌንሶች የተገጠሙለት ሲሆን፤ ሌንሶቹም 50 ሜጋ ፒክስል፣ 13 ሜጋ ፒክሰል እና 12 ሚክስል ናቸው።
ከፊትለፊት አሊያም ሰለፊ ካሜራው ደግሞ 1 ሲሆን፤ የሌንሱ ምስል የማንሳት ጥራትም 13 ሜጋ ፒከስል ነው ተብሏል።