በእግር ኳስ ሊዮኔል ሜሲ በባላንዶር ለ8ኛ ጊዜ መንገስ ችሏል
ለመጠናቀቅ ቀናት በቀሩት የፈረንጆቹ በ2023 ዓለማችን አትሌቲክስ እና እግር ኳስን ጨምሮ በርካታ ስፖርታዊ ሁነቶችን አሰተናዳለች።
በአትሌቲክስ ኢትዮጵያውን አትሌቶች በተለያዩ መድረኮች መንገስ የቻሉ ሲሆን፤ በእግር ኳሱ ዘርፍም ሜሲ፣ ክርስቲያኖ ሮናዶ፣ ምባፔ እና ሃላንድ ስማቸው የገነነ ተጫዋቾች ነበሩ።
አትሌቲክስ በ2023
በመገባደድ ላይ በሚገኘው የፈረንጆቹ 2023 የዓለም አትሌቲክስ ሻፒዮናን ጨምሮ በርካታ የትራክ እና የጎዳና ላይ ውድድሮች የተካሄዱ ሲሆን፤ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም የሀገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርገው አውለብልበዋል።
ቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና
የቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያ 2 የወርቅ፣ 4 የብርና 3 የነሃስ በድምሩ 9ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም 6ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 2ኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቋ ይታወሳል።
በውድድሩ ላይ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር እንዲሁም አትሌት አማኔ በሪሶ በሴቶች ማራቶን ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝተዋል።
ሻምፒዮናውን አሜሪካ በ29 ሜዳሊያ ከዓለም አንደኛ ደረጃን በመያዝ ስታጠናቅቅ፣ ካናዳ እና ስፔን ሁለተኛ ና ሶስተኛ ደረጃን መያዝ ችለዋል።
ሪጋ የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ
ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክ የጎዳና ላይ ውድድር ኢትዮጵያ 2 የወርቅ፣ 4 የበር እና 1 የነሃስ በድምሩ 7 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም 2ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀችበት ነበር።
በሻፒዮናው ላይ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድርቤ ወልተጂ ወልተጂ በ1 ማይል የጎዳና ላይ ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ሰብራለች።
ሪጋ የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫን ኬንያ በ5 የወርቅ፣ 3 የብር እና 4 የነሃስ በድምሩ በ12 ሜዳሊያዎች ከዓለም አንደኛ በመያዝ አጠናቃለች።
ክብረወሰን እና የኢትዮጵያ አትሌቶች
ለመጠናቀቅ ቀናት በቀሩት የፈረንጆቹ 2023 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በትራክ እና በጎዳና ላይ ውድድሮች የዓለም ክብረወሰኖችን በእጃቸው ማስገባት የቻሉበት ዓመትም ነበር።
አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ፤ የዓለም ክብረወሰን በእጃቸው ካስገቡ አትሌቶች መካከል ትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ አንዷ ስትሆን አትሌቷ የ5000 ሜትር 14:00.21 በሆነ ሰዓት በመግባት የክብረወሰን ባለቤት መሆን ችላለች።
አትሌት ለሜቻ ግርማ፤ የ3000ሺ ሜትር የመሰናልክ ውድድር ለሜቻ የርቀቱ የክብረወሰን ባለቤት መሆን የቻለ ሲሆን፤ ለሜቻ 7:52:11 በመግባት የርቀቱን አዲስ የአለም ሪከርድ አስመዝግቧል።
አትሌት ትእግስት አሰፋ፤ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትግስት አሰፋ የበርሊን ማራቶን የሴቶችን የአለም ክብረወሰን መስበር ችላለች። ግስት 2 ሰአት፣ ከ11 ደቂቃ፣ ከ53 ሰከንድ ነው ውድድሩን ያጠናቀቀች ሲሆን፤ በኬንያዊቷ ብርጊድ ኮስጊ በ2:14:04 ሰአት ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን ከ2 ደቂቃ በላይ በማሻሻል ሰብራዋለች።
በተጨማሪም አትሌት ትእግስት አሰፋ የ2023 ከስታዲየም ውጪ በተደረጉ ውድድረፖች የዓለም ምርጥ ሴት አትሌት ሽልማትንም አሸንፋለች።
አትሌት ድርቤ ወልተጂ፤ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ1 ማይል የጎዳና ላይ ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ሰብራለች።
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፤ ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ውድድር የተመለሰው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የቫሌንሽያ ማራቶን 4ኛ ሆኖ ቡያጠናቅቅም፤ ያስመዘገበው ሰዓት 2: 04: 19 ከ40 ዓመት በላይ የዓለም ማራቶን ክብረወሰን ሆኖ ተመዝግቧል።
እግር ኳስ
2023 ዓመት በእግር ኳሱ ዓለም ከባላንድር እስከ አነጋጋሪው የሴቶች የዓለም ዋንጫ፤ ከእንግዚልዝ ፕሪምየር ሊግ እስክ ሳዑዲ ፕሮ ሊግ የተለያዩ አነጋጋሪ እና ስገራሚ ክስተቶችን አስተናግዶ አልፏል።
ኢትዮጵያ
አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣን ሆነው የተቀጠሩት በዚሁ ዓመት ነው። በወርሃዊ ደመወዝ 250 ሺህ ብር የተቀጠሩት አሰልጣኙ ሁለት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል።
የሴቶች የዓለም ዋጫ
አውስትራሊያ እና ኒውዝላንድ በጋራ ያስተናገዱት የሴቶች ዓለም ዋንጫ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 32 ብሄራዊ ቡድኖች የተሳተፉበት ሲሆን በስፔን አሸናፊነት መጠናቀቁም ይታወሳል።
የሰፔን እግር ኳስ ፌደሬሽን ኃላፊ የዓለም ዋንጫ ድልን እያከበሩ በነበረበት ሰአት የተጫዋች ጀኒ ሄርሞሶን ከንፈር ሳታስብበት መሳማቸው ቁጣ መቀስቀሱም የዘንድሮ የሴቶች የዓለም ዋንጫ ክስተት ሆኖ አልፏል።
ባላንድኦር
አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ 8ኛውን የባሎንዶር ሽልማት ማሳከት ችሏል። በኳታር ሀገሩን ከ1986 በኋላ ሻምፒዮን ያደረገው ሜሲ ከ2021 በኋላ ሽልማቱን ዳግም በእጁ አስገብቷል።
ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ሶስት ዋንጫዎችን ያነሳውና በውድድር አመቱ 56 ጎሎችን ያስቆጠረው ኧርሊንግ ሃላንድ የአመቱ ምርጥ ጎል አስቆጣሪ ክብርን ተቀዳጅቷል።
አርጀንቲናዊው የአስቶንቪላ ግብ ጠባቂ ኢሚሊያኖ ማርቲኔዝ ደግሞ የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ሆኖ በመመረጥ ሽልማቱን ወስዷል።
እንግሊዛዊው አማካይ ጁድ ቤሊንግሃም የ2023 የአለም ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል።
በሳኡዲ ፕሮ ሊግ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ሳዑዲ ማቅናቱን ተከትሎ በ2023 የሳዑዲ ፕሮ ሊግ የዓለም ትኩረትን መሳቡን አንደቀጠለ ነው።
በፈረንጆቹ 2023 ብቻ የሳኡዲ ክለቦች ከኔይማር እስከ ቤንዜማ፤ ከፊርሚኖ እስከ ሳዲዮ ማኔ በአውሮፓ ሊጎች የደመቁ ተጫዋቾችን ማስፈረም ችለዋል። ኔይማር ጁኒየር አል ሂላልን መቀላቀሉን ተከትሎ በሳኡዲ ሊጎች የሚጫወቱ ብራዚላዊያንን ቁጥር 25 አድርሷል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ሜሲ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ፤ የ38 ዓመቱ ፖርቹጋላዊ የእግር ኳስ ኮከብ ከሳዑዲውን አል ናስር ጋር በመሆን አሁንም ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል።
ሊዮኔል ሜሲ፤ አርጀንሪናዊው ኮክብ ሊዮኔል ሜሲም ወደ አሜሪካው ኢንተር ሚያሚ የእግር ኳስ ከልብን የተቀላቀለ ሲሆን፤ በክለቡም ይሁን በአሜሪካ ሊግ ከፍተኛ መነቃቃትን ፈጥሯል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከሜሲ ጋር የነበረው ፉክክር ማብቃቱን ያወሰወቀውም በመገባደድ ላይ በሚገኘው በፈረንጆቹ በ2023 ነው።
ሮናልዶ፤ እኔ እና ሜሲ የእግር ኳስ መድረኩን ለ15 ዓመታት ተጋርተናል፤ ጓደኛሞች ነን አልልም ግን እርስ በርሳችን እንከባበራለን” ብሏል።
ሁለቱም ተጫዋቾች የእግር ኳስን ታሪክ ቀይረዋል እና ክብር ይገባቸዋል ሲል የገለጸው ሮናልዶ፤ አሁን ላይ በክርሲያኖ ሮናልዶ እና በሜሲ መካከል ያለው የፉክክር ዘመን አብቅቷል ሲልም አስታውቋል።
አሳዛኝ ክስተት በእግር ኳስ
የ28 ዓመቱ ጋናዊው ራፋኤል ድዌሜና እግር ኳስ እየተጫወተ እያለ ህይወቱ ማለፉ በፈረንጆቹ 2023 እግር ኳስ ያጋጠመ አሳዛኝ ክስተት ነበር።
ጫዋቹ ለአልባኒያ ሱፐርሊግ ተሳታፊው ኢግናቲያ ክለብ ከፓርቲዛኒ ጋር እየተጫወተ እያለ በ23ኛው ደቂቃ ላይ ከወደቀ በኋላ ህይወቱ አልፏል ተብሏል።