የሜታ ንብረት የሆኑ መተግበሪያዎችንም ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን በላይ ሰዎች ጭነውቸዋል
ሊጠናቀቅ በጣት የሚቆጠሩ ቀናት በቀረው 2023 የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሚጠቀሙ ቲክኖሎጂዎች ቀደምቶቹን የማህበራዊ ትስስር ገጾች ተፈታትነዋል።
የኦፕንኤአይ ንብረት የሆነው ቻትጂፒቲን ጨምሮ የጎግሉ ባርድ እና የማይክሮሶፍቱ ኮ ፓይለት መተግበሪያዎች በስፋት አገልግሎት ላይ ውለዋል።
በ2023 ከጎግል ፕሌይ አልያም አፕ ስቶር ላይ በርካታ ሰዎች ያወረዷቸው መተግበሪያዎች ግን የቀደሙት ታዋቂ የማህበራዊ ትስስር ገጽ መተግበሪያዎች ናቸው።
በዚህ አመት አጠቃላይ ተጠቃሚዎቹ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን የደረሱለት ቲክቶክ በ2023 የመጀመሪያ አጋማሽ ብቻ 672 ሚሊየን ሰዎች አውርደውታል።
የሜታ ንብረት የሆኑት ኢንስታግራም፣ ፌስቡክ እና ዋትስአፕም በድምሩ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን በላይ ሰዎች የጫኗቸው መተግበሪያዎች በመሆን አሁንም አለማቀፍ ተቀባይነታቸው ጉልህ መሆኑን አሳይተዋል።
ስታቲስታ በ2023 በብዛት የተጫኑ ናቸው ብሎ ያወጣቸው 10 መተግበሪያዎች ቀጥሎ ቀርበዋል፦