ውድድሩ ከጥር 4 ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት በስድስት ስታዲየሞች ይካሄዳል
ከአንድ ሳምንት በኋላ በኮቲዲቯር የሚጀመረው የአፍሪካ ዋንጫ አዳዲስ ነገሮች
34ኛው የአፍሪካ ወንዶች አግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ከጥር 4 እስከ የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
ተወዳጁ የአፍሪካ ዋንጫ ከጥር 4 ጀምሮ ለአንድ ወር የሚካሄድ ሲሆን አዘጋጇ ኮቲዲቯር ስድስት ስታዲየሞችን አዘጋጅታለች፡፡
ምዕራብ አፍሪካዊቷ ኮቲዲቯር የአፍሪካ ዋንጫን ለመጨረሻ ጊዜ ያዘጋጀችው ከ40 ዓመት በፊት በ1984 ዓመት ላይ የነበረ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫን ታዘጋጃለች፡፡
የውድድሩ መክፈቻ ጨዋታ 60 ሺህ ደጋፊዎችን በሚይዘው በአላሳን ኦታራ ስታዲያም ከአንድ ሳምንት በኋላ ቅዳሜ ዕለት በኮቲዲቯር እና ጊኒ ቢሳው ይጫወታሉ፡፡
በአጠቃላይ ሀገሪቱ ስድስት ስታዲየሞችን ለውድድሩ ያዘጋጀች ሲሆን በአላሳን ኦታራ ስታዲያም፣ ፌሊክስ ቦኚ ስታዲያም፣ አልሳሌም ስታዲየም፣ አማዱ ጆን ኩሊባሊ ስታዲየም፣ ሎውሬንት ባኩ እና ቻርልስ ካነን ቢውልደር ስታዲየም ደግሞ ጨዋታዎቹ የሚካሄዲባቸው ስፍራዎች ናቸው፡፡
እነዚህ ስድስት ስታዲየሞች ከ20 ሺህ እስከ 60 ሺህ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ያላቸው ሲሆን የመክፈቻው እና የዋንጫ ጨዋታዎች በአላሳን ኦታራ ስታዲያም ይካሄዳሉ ተብሏል፡፡
ለ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸውን ያረጋገጡ ሀገራት
በዚህ ውድድር ላይ ግብጻዊው መሀመድ ሳላህ፣ ናይጀሪያዊው አጥቂ ቪክተር ኦስሜን፣ የጊኒው ሰርሁ ጉራሲ፣ ጋናዊው ሞሃመድ ኩዱስ፣ የቡርኪናፋሶው ኢሳ ካቦሬ እና የሞሮኮው አዘዲን ኦናሂ በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ይደምቃሉ ተብለው ከተለዩ ተጫዋቾች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡
የውድድሩ ባለቤት የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ውድድሩን የሚዳኙ ከ32 ሀገራት የተውጣጡ ዳኞችን ዝርዝር ይፋ ያደረገ ሲሆን የተንቀሳቃሽ ምስል ዳኝነት ወይም ቫርን ጨምሮ 68 ዳኞችን ይፋ አድርጓል፡፡