2024 ሞቃታማ አመት ሆኖ በሪከርድነት ተመዘገበ
"ደብሊው ኤምኦ 2024 ሞቃታማ አመት መሆኑን ይፋ ያደርጋል" ሲሉ ቃል አቀባይዋ በጀኔቫ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል
የአለም ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ባደረጓቸው የኮፕ ስብሰባዎች የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ትኩረት የሚያሻው አለምአቀፍ አጀንዳ እንዲሆን ተስማምተዋል
2024 ሞቃታማ አመት ሆኖ በሪከርድነት መመዝገቡን የአየም የሜትሮሎጂካል ድርጅት አስታወቀ።
2024 ሞቃታማ አመት ሆኖ በሪከርድነት መመዝገቡን የአለም የሜትሮሎጂካል ድርጅት(ደብሊው ኤም ኦ) ቃል አቀባይ በርካታ ቀጣናዊ የአየር ንብረት ተቆጣጣሪ ተቋማት ግኝት የያዙ አጠቃላይ ሪፖርት ከመውጣቱ ዛሬ ከመለቀቁ ቀደም ብለው ተናግረዋል።
ቃል አቀባይዋ ክሌር ኑሊስ እንደገለጹት ይፋ ይሆናል የተባለው የጥናት ግኝት በበርሊን፣ ቻይና፣ አውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ ያሉ የአየር ንብረት መከታተያዎችን ግኝት ያካትታል።
"ደብሊው ኤምኦ 2024 ሞቃታማ አመት መሆኑን ይፋ ያደርጋል" ሲሉ ቃል አቀባይዋ በጀኔቫ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ቃል አቀባይዋ አክለውም "እጅግ የተለየ የመሬት እና የባህር ገጽ ሙቀት እና የተለየ የውቅያኖስ ሙቀት አይተናል። ከባድ የአየር ሀኔታዎች ህይወት፣ ንብረትና ተስፋ በማሳጣት በመላው አለም በርከታ ሀገራትን አጥቅተዋል" ብለዋል።
የአለም ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ባደረጓቸው የኮፕ ስብሰባዎች የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ትኩረት የሚያሻው አለምአቀፍ አጀንዳ እንዲሆን ተስማምተዋል።
በአረብ ኢምሬትስ ዱባይ በተካሄደው የኮፕ28 የተመድ የአየር ንብረት ጉባኤ ሀገራት ታዳሽ ያልሆነ ወይም ነዳጅ ዘይትም ለመቀነስ እና በምትኩ በታዳሽ ኃይል ላይ መጠነሰፊ ኢንቨስትመንት ለማድረግ መስማማታቸው ይታወሳል። በአርባጃን በተካሄደው ኮፕ 28 ደግሞ ያደጉ ሀገራት በማደግ ያሉ ሀገራት ለሚያከናውኗቸው የአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ ጥረቶች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።