በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ክርክር ትራምፕ በባይደን ላይ የበላይነትን ተቀዳጅተዋል
የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ደካማ የክርክር ብቃት ዴሞክራችን አስደንግጧል
በተሰበሰበ የህዝብ አስተያየት ትራምፕ 67 በመቶ ድምጽ ማግኘት ክርክሩን በሰፊ ልዩነት አሸንፈዋል
ለ2024ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሚፎካከሩት ጆ ባይደን እና ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ምሽት የመጀመሪያውን የፊት ለፊት ክርክራቸውን አድርገዋል።
በሴኤንኤን አዘጋጅነት በተደረገው የአሜሪካ የፕሬዝዳንታዊ ተፎካካሪወች ክርክር ለ90 ደቂቃ የቆየ ሲሆን፤ ክርክሩን የሪፕሊካኑ ተወካይ ዶናልድ ትራምፕ የበላይነት የያዙበት ነው ተብሏል።
ፕሬዝዳንት ባይደን አቅማቸውንና አለመድከማቸውን ሊያሳዩ፤ ገና ሌላ የስልጣን ዘመንን የመምራት አካላዊና አእምሯዊ ብቃት እንዳላቸው ሊያስመሰክሩ ነበር ያለሙት ።
ያም ሆኖ ጆ ባይደን በ2024 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ የመጀመሪያው የቴሌቭዥን ክርክር የ90-ደቂቃ ፍልሚያ ላይ ደካማ አፈጻጸም አሳይቷል ነው የተባለው።
ጆ ባይደን ድምጻቸው ደክሞ፣ በራስ መተማመናቸው ጠፍቶ፣ አቀርቅረው፣ ሃሳባቸው ተበትኖና አንደበታቸው ተሳስሮ ነበር ክርክሩን የጨረሱት።
በክርክሩ ወቅት ትራምፕ ባይደንን በኢኮኖሚው እና በውጭ ፖሊሲ ላይ ደጋግመው ያጠቁ ሲሆን፤ ባይደን በአንጻሩ በተፎካካሪያቸው የወንጀል ክስ እና የ 2020 ምርጫን ለመቀልበስ ሙከራዎች በመናሳት አጥቅተዋል።
ባይደን ትራምፕን “ተሸናፊ እና “የዱር ድመት ሞራል” ያለው ሰው ነው ሲሉ ዘልፈዋቸዋል።
ትራምፕ በምላሹም፤ በባይደን ስህተቶች ላይ ተንተርሰው፤ ባይደንን ሃሳባቸው ግልጽ ያልሆነ፣ ከህዝብ እሳቤና ችግር የታፋቱ አድርገው አቅርበዋቸዋል።
በክርክሩ ማብቂያ ላይ በተሰበሰበ የህዝብ አስተያየት ትራምፕ 67 በመቶ ባይደን ደግሞ 33 በመቶ ድምጽ በማግኘታቸው ትራምፕ ክርክሩን በሰፊ ልዩነት ማሸነፋቸውን አሳይተዋል።
ዴሞክራቶች በፕሬዚዳንቱ አፈጻጸም ላይ ስጋታቸውን ገልጸዋል የተባለ ሲሆን፤ የፓርቲው የውስጥ አዋቂዎች ቀደም ሲል የሰጡት መልሶች ፍርሃትን እንዳጫረባቸው ተናግረዋል።
ሆኖም ግን ምክትል ፐሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ "በዝግታ የተጀመረ፣ ነገር ግን ጠንካራ አጨራረስ የነበረው" ሲሉ ለባይደን ወገንው ተከራክረዋል።
የ81 አመቱ የዴሞክራት እጩ ጆ ባይደን እና የ78 አመቱ ሪፐብሊካን ዶናልድ ትራምፕ በ2020 ሁለት ጊዜ የፊት ለፊት ክርክር አድርገዋል።