ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ዶናልድ ትራምፕ በክርክር ወቅት ማይክ ለማጥፋት ተስማሙ
ሁለቱ የአሜሪካ እጩ ፕሬዝዳንቶች የፊት ለፊት ክርክር ለማድረግ በብዙ ቅድመ ሁኔታዎች ለማድረግ መስማማታቸው ይታወሳል
ሁለቱ መሪዎች ከሁለት ሳምንት በኋላ በሲኤንኤን ስቱዲዮ ያለ ተመልካች ይከራከራሉ ተብሏል
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ዶናልድ ትራምፕ በክርክር ወቅት ማይክ ለማጥፋት ተስማሙ፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ በቀጣዩ ዓመት ሕዳር ወር ላይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደምታደርግ ይታወቃል፡፡
በዚህ ምርጫ ለይ በስልጣን ላይ የሉት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዲሁም ሮበርት ኬነዲ ጁኒየር የግል ዕጩ ሆነው ይቀርባሉ፡፡
ሁለቱ ዋነኛ የዲሞክራት እና ሪፐብሊካን ፓርቲ እጩዎች ከሁለት አንዳቸው ምርጫውን እንደሚያሸንፉ የተገመተ ሲሆን እጩዎቹ በተደጋጋሚ የሚያደርጓቸው የእርስ በርስ ጉንተላዎች ምርጫውን የበለጠ አጓጊ አድርጎታል፡፡
የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ በተደጋጋሚ በስልጣን ላይ ካሉት ተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን ጋር የፊት ለፊት ክርክር ለማድረግ ሲጠይቁ ቆይተዋል፡፡
ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩት እና በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ ክርክሩን ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ሲሉ ማለታቸውን ተከትሎ ሰኔ 20 ቀን 2016 ዓ.ም አትላንታ በሚገኘው የሲኤንኤን ስቱዲዮ ለመከራከር ተስማምተዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ስምንት እጩ ምክትል ፕሬዝዳንቶችን አጩ
እጩዎቹ በክርከሩ ወቅት አንዳቸው የአንዳቸውን ንግግር ላለማቋረጥ እንደተስማሙ ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሁለቱ እጩዎች ያለ ተመልካች በዝግ አዳራሽ ክርክሩን ለማድረግ ነገር ግን ሙሉ ክርክራቸው በሲኤንኤን እንደሚተላለፍ ተገልጿል፡፡
በአሜሪካ የምርጫ ህግ መሰረት ሚዲያዎችን ዋነኛ እጩዎችን ክርክር እንዲያደርጉ ለማድረግ ቢያንስ የ270 መራጮችን ድምጽ ማግኘታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
በዚህ መሰረት ሮበርት ኬኔዲ ጁኒየር የተሰኘው እጩ ፕሬዝዳንት ተወዳዳሪ እስካሁን ማግኘት ያቸለው 89 ድምጽ ብቻ ነው የተባለ ሲሆን በክርክር መድረኩ ላይ ላይሳተፍ እንደሚል ከወዲሁ ተገምቷል፡፡