ክርስቲና ኦዝሩክ የ105 ልጆች እናት መሆን እንደምትፈልግ አስታውቃለች
የ26 ዓመቷ ሩሲያዊት እናት ክርስቲና ኦዝሩክ የ22 ልጆች እናት መሆን መቻሏን አስታውቃለች።
በጆርጂያ የምትኖረው የ26 ዓመቷ ሩሲያዊት እናት ክሪስቲና ኦዝቱርክ 21 ልጆቿን በማህጸን ኪራይ አማካኝት ያገኘች ሲሆን፤ 20ዎቹ በአንድ አመት ውስጥ በፈረንጆቹ 2020 ተወልደዋል።
የክርስቲና ኦዝሩክ የመጀመሪያ ልጅ 8 ዓመቷ ሲሆን፤ በቀደመ የፍቅር ግንኙነቷ በተፈጥሯዊ መንገድ የተወለድ መሆኑን የዴይሊ ሜይል ዘገባ ያመለክታል።
ቀሪዎቹ 21 ልጆቹ በኪራይ ማህጸን የተወለዱ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ከአንዱ በስተቀር ሁሉም በአንድ ዓመት ውስጥ የተወለዱ መሆኑ ተነግሯል።
በአሁኑ ጊዜ በጆርጂያ የምትኖረው ሩሲያዊት እናት ሚሊየነር ከሆነው ባለቤቷ ጋር እስከ 105 የሚደርሱ ባዮሎጂያዊ ልጆች እንዲኖራት እንደምትፈልግ ተናግራለች።
የለጆቹ አባት የሆነው የ58 ዓመቱ ሚሊየነር ጋሊፕ ኦዝትሩክ፤ በአደንዛዥ እጽ ዝውውር ጋር በተያያዘ የ8 ዓመት እስር እንደተፈረደበት ተነግሯል።
ሆኖም ግን ጥንዶቹ ማህጸናቸውን በሚያከራዩ ሴቶች አማካነት ልጆችን መውለደቸውን ቀጥለዋል የተባለ ሲሆን፤ በእስር ቤት ውስጥ ሆኖም ልጆች መውለዳቸውን እንደሚቀጥሉ ነው የተገለጸው።
የልጆቹ እናት ክረስቲና እንደተናገረችው፤ በፈረንጆቹ ከመጋቢት 2020 እስከ ሀምሌ 2021 ድረስ ለማጸን ኪራይ ብቻ 142 ሺህ ዩሮ ከፍለዋል።
ቤተሰቡ አሁን ላይ ልጆቹን የሚንከባከብ 16 ሞግዚቶች የተቀጠሩለት ሲሆን፤ ለሞግዚቶቹም በዓመት 68 ሺህ ዩሮ እንደሚከፈልም ነው የተገለጸው።