በላይቤሪያ በቤተክርስቲያን ውስጥ በተፈጠረ መገፋፋት የ29 ሰዎች ህይወት አለፈ
የግርግሩ መንስኤ ምን እንደሆነ አልገለጸም ተብሏል
የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ቦታውን እንደሚጎበኙ የፕሬዝዳንቱ የፕሬስ ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል
በትናንትናው እለት በላይቤሪያ ዋና ከተማ ሞንሮቪያ በቤተክርስቲያን ውስጥ በነበሩ ሰዎች በተፈጠረ መገፋፋት ምክንያት የ29 ሰዎች መሞታቸውን ምክትል የማስታወቂያ ሚኒስትሩ መናራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
አደጋው የተከሰተው በዋና ከተማው ዳርቻ ላይ በምትገኘው በኒው ክሩ ታውን ሌሊቱን ሙሉ በክርስቲያናዊ አምልኮ ዝግጅት ወቅት ነው ሲሉ ምክትል የማስታወቂያ ሚኒስትር ጃላዋ ቶንፖ ገልጸዋል፡፡ ተናግረዋል።
የግርግሩ መንስኤ ምን እንደሆነ አልገለጸም ተብሏል።
“ዶክተሮቹ 29 ሰዎች መሞታቸውን እና አንዳንዶቹም በጽኑ መጎዳታቸውን ተናግረዋል” ሲል ቶንፖ በአቅራቢያው ከሚገኝ ሆስፒታል የመንግስት ሬዲዮ ጋር ደውሏል፡፡
"ይህ ቀን ለሀገሪቱ አሳዛኝ ነው"
ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ቦታውን ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የፕሬስ ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።