ከጠቅላላው የአውሮፓ ህዝብ ውስጥ 21 በመቶ በድህነት የሚኖር ነው ተብሏል
38 በመቶ አውሮፓዊያን በቀን ሶስቴ ምግብ የመብላት አቅም እንደሌላቸው ተገለጸ፡፡
742 ሚሊዮን የህዝብ ብዛት ያለው አውሮፓ 104 ትሪሊዮን ሀብት በመያዝ ከሁሉም አህጉራት ሀብታሙ አህጉር በመባል ይታወቃል፡፡
የአውሮፓ ባሮሜትር ይፋ ባደረገው ጥናት መሰረትም 38 በመቶ የአህጉሪቱ ህዝቦች በቀን ሶስት ጊዜ የመብላት አቅም እንደሌላቸው ገልጿል፡፡
በሁሉም የህብረቱ አባል ሀገራት ካሉ 10 ሺህ ዜጎች በዚህ ጥናት ላይ ተሳትፈዋል የተባለ ሲሆን በጥናቱ ከተሳተፉት ውስጥ 15 በመቶዎቹ ብቻ የኑሮ ውድነት እና የምግብ ዋጋ መናር አያሳስበንም ብለዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ በየዓመቱ እየናረ የመጣው የነዳጅ እና ምግብ ዋጋ ህይወታቸውን እየፈተነው ነው ያሉ ሲሆን በተለይም ችግሩ እየሰፋ የመጣው ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ ነው፡፡
በጥናቱ መሰረትም 29 በመቶ አውሮፓዊያን የገንዘብ አቅማቸው አደጋ ውስጥ ወድቋል የተባለ ሲሆን ከሁለቱ አውሮፓዊያን አንዱ በቀጣዮቹ ወራት ውስጥ ወደ ገንዘብ ቀውስ የመግባት አደጋ አንዣቦባቸዋልም ተብሏል፡፡
ከዚህ በፊት በተደረገ ጥናት 17 በመቶ አውሮፓዊያን የድህነት አደጋ ውስጥ ሲሆኑ ከ75 በመቶ በላይ አውሮፓዊያን ደግሞ በዋጋ መናር ምክንያት የገንዘብ አጠቃቀማቸውን ለማመጣጠን መገደዳቸውን ተናግረዋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አሳስበኛል አለ
በብሪታንያ 6 ሚሊዮን ገደማ ዜጎች ዝቅተኛ ገቢ አላቸው የተባለ ሲሆን ምግብ እና መሰል መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ማሟላት እማይችሉበት ደረጃ ላይ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡
እነዚህ በድህነት ውስጥ የሚኖሩ አውሮፓዊያን የምግብ ፍላጎቶቻቸውን ለመሸፈን ቅናሽ ያላቸው የምግብ ባንክ እና ሌሎች ማህበራትን እየፈለጉ ነውም ተብሏል፡፡
በአጠቃላይ በኑሮ ውድነቱ ምክንያት በቀን ሶስቴ እየተመገቡ ያሉት 42 በመቶ የአህጉሪቱ ነዋሪዎች ብቻ ናቸው የተባለ ሲሆን 21 በመቶዎቹ ደግሞ ልጆቻቸውን ለመመገብ ሲሉ ቢያንስ አንድ ጊዜ የግድ መመገብ እንደሚያቆሙ በጥናቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡