ፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪ ተቀጣሪዎች በህብረቱ እየተገፉ ነው ተብሏል
ፈረንሳይ በአውሮፓ ህብረት የስራ ቋንቋ ዙሪያ ተቃውሞዋን ገለጸች፡፡
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እንዳሉት የአውሮፓ ህብረት ከተቀመጠለት ህግ እና የሀገራት ስምምነት ውጪ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
በኡረሱላ ቮንደርሊን የሚመራው የአውሮፓ ህብረት ለእንግሊዘኛ ተናጋሪዎች ያደላል የሚል ክስ የቀረበበት ሲሆን በተለይም በሰራተኛ ቅጥር ዙሪያ ፈረንሳይኛ ተናጋሪዎች እየተገፉ ነው ተብሏል፡፡
እንደ ዴይሊ ሜይል ዘገባ ከሆነ የአውሮፓ ህብረት ለሁሉም የህብረቱ የስራ የቋንቋ ተናጋሪዎች ከአድልዎ የጸዳ አገልግሎት ለመስጠት የተጣለበትን ሀላፊነት ጥሷል፡፡
በተለይም በህብረቱ ስር ያሉ የጠፈር ሳይንስ፣ መከላከያ እና ኢኮኖሚክስ የሀላፊነት ቦታዎች በእንግሊዘኛ ተናጋሪዎች የበላይነት መያዙን ፈረንሳይ ገልጻለች፡፡
የህብረቱን ኢ ፍትሀዊ አካሄድን ለመግታት በማለምም ፈረንሳይ በህብረቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መስርታለች ተብሏል፡፡
በኒጀር ያለው የፈረንሳይ እና አሜሪካ ጦር በእገታ ላይ ያሉትን ፕሬዝዳንት ለመታደግ ጥቃት ይከፍት ይሆን?
እንደ ፕሬዝዳንት ማክሮን ገለጻ የጽሁፍ ፈተናዎች በእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቻ እንዲሰጡ ማድረግ ከህግ ጥሰቶች መካከል አንዱ ሲሆን ይህም የሕብረቱን መተዳደሪያ ደንብ እንደሚጥስ ተገልጿል፡፡
ከፈረንሳይ ባለፈ ጣልያንም ተቃውሞዋን በህብረቱ ላይ ካሰሙ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ለፈረንሳይ ድጋፏን አሳይታለች ተብሏል፡፡
በአውሮፓ ህብረት የፈረንሳይ ቋንቋ አለመፈለግ ስሜት ለፓሪስ ተጽዕኖ ፈጣሪነት መቀነስ ጋር እየተያያዘ ሲሆን ፕሬዝዳንት ማክሮን እየተተቹበትም ይገኛል፡፡