በህንድ እየተገነባ ያለ ዋሻ የተደረመሰባቸውን 40 ሰዎች ነፍስ ለማዳን ትንቅንቅ እየተደረገ ነው
ከመንግስት እና ከትምህርት ተቋማት የተውጣጣ የዲኦሎጂስቶች ቡድን አደጋው የተከሰተበትን ምክንያት ለማወቅ ቦታው ላይ ደርሷል
የነፍስ አድን ሰራተኞች ፍርስራሹን በማስወገድ መውጫ አጥተው ያሉትን ሰራተኞችን በህይወት ለማትረፍ ለሁለት ቀናት ያለእረፍት እየሰሩ ናቸው
በህንድ እየተገነባ ያለ ዋሻ የተደረመሰባቸውን 40 ሰዎች ነፍስ ለማዳን ትንቅንቅ እየተደረገ ነው ተባለ።
በህንድ ኡታራካንድ ግዛት የሚገኝ የመሬት ውስጥ የመንገድ ዋሻ የተደረመሰባቸውን 40 የግንባታ ሰራተኞች በህይወት ለማትረፍ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
ይህ 3 ማይል የሚረዝመው ዋሻ የመደርመስ አደጋ ያጋጠመው ባለፈው እሁድ መሆኑን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
የነፍስ አድን ሰራተኞች ፍርስራሹን በማስወገድ መውጫ አጥተው ያሉትን ሰራተኞችን በህይወት ለማትረፍ ለሁለት ቀናት ያለእረፍት እየሰሩ ናቸው።
ሰራተኞቹን በህይወት ለማውጣት ፍርስራሹን በጥንቃቄ እያወጡ መሆናቸውን ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።
እየተንጠባጠበ ያለው ፍርስራሽ እንቅፋት እንደሆነባቸው የገለጹት ባለስልጣናቱ ማክሰኞ ሌሊት ወይም ሮብዕ ሰራተኞቹን በህይወት ማውጣት ይቻላል የሚል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
የዲሳስተር ማኔጅመንት ባለስሌጣን የሆኑት ዴቨንድራ ሲኝ ፖትዎል "መውጣት ላልቻሉት ሰራተኞች እና የስራ ኃላፊዎች ምግብ፣ ውሃ እና ኦክስጅን እያቀረብንላቸው ነው" ብለዋል።
ከመንግስት እና ከትምህርት ተቋማት የተውጣጣ የዲኦሎጂስቶች ቡድን አደጋው የተከሰተበትን ምክንያት ለማወቅ ቦታው ላይ ደርሷል።
በዋሻው ውስጥ ከ50-60 የሚሆኑ ሰራተኞች የነበሩ ቢሆንም 10-20 የሚሆኑት የስራ ፈረቃቸው በማለቁ አደጋው ሳይከሰት ወጥተዋል ተብሏል።
የመንገድ ግንባታው በግዛቱ ያሉ የሂንዱ ቴምፕሎችን ለማገናኘት ያለመ የመንግስት ፕሮጀክት አካል መሆኑ ተገልጿል።