ዝቅተኛ እርጥበት እና ቀዝቃዛ ንፋስ ጫማው እንዳይበላሹ አድርጓል ተብሏል
ተመራማሪዎች የአውሮፓ በእድሜ ትልቁ ያሉትን ነጠላ ጫማ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ቢቢሲ እንደዘገበው በስፔን ዋሻ የተገኙት ጫማዎች፤ የስድስት ሽህ ዓመት እድሜ እንዳላቸው ተገምቷል።
በሌሊት ወፍ ዋሻ ከተገኙት በርካታ ጥንታዊ ቁሶች መካከል ነው የተባሉት ጫማዎቹ፤ በ19 ክ/ዘመን በማዕድን አውጭው ተወስደው እንደነበር በጥናት ተለይቷል።
በዋሻው ውስጥ ዝቅተኛ እርጥበት እና ቀዝቃዛ ንፋስ ጫማዎቹ እንዲጠበቁና እንዳይበላሹ አድርጓቸዋል ተብሏል።
ነጠላ ጫማዎቹ በአሰራራቸው የተለዩና የሳር አይነቶችን እንደተጠቀሙ ተመራማሪዎች ገልጸዋል። ነገር ግን እንደ ቆዳ ያሉ ሌሎች ቁሳቁሶችም ጫማውን ለመስራት ጥቅም ላይ መዋላቸውን ተናግረዋል።
በአዲሱ የድጋይ ዘመን (በኒዮሊቲክ ዘመን) ተሰርተዋል የተባለም ሲሆን፤ በፈረንጆቹ 2008 በአርሜኒያ ዋሻ ውስጥ ከተገኘው ከአምስት ሽህ 500 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ የቆዳ ጫማ በላይ እድሜ ያላቸው ናቸው።
ተመራማሪዎቹ ዋሻውን ለመጀመሪያ ጊዜ በ1831 የመሬቱ ባለቤት ማዳበሪያን ለማምረት ይጠቀሙበት ነበር ብለዋል።