40ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
በጉባዔው የህብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና የልዩ ልዩ ተቋማት ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው
የአስፈጻሚ ምክር ቤቱ ለ35ኛው የመሪዎች ጉባኤ ላይ በሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል
40ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በጉባኤው የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የህብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና የልዩ ልዩ ተቋማት ኃላፊዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
40ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ“የአፍሪካ አህጉርን የስርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፣ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን ማፋጠን” በሚል መሪ ቃል ነው በመካሄድ ላይ ያለው።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ክቡር ሙሳ ፋኪ መሃመት ባደረጉት ንግግር፤ የኮሮና ቫይረስ የፈጠረው ተፅዕኖ እና ለመቋቋም እየተደረገ ስላለው ጥረት፣ የአጀንዳ 2063 የአፈጻጸም ሂደት፣ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና አተገባበር እንቅስቃሴ እና መሰል ወቅታዊ የአህጉሪቷን አጀንዳዎች አንስተዋል።
የአስፈጻሚ ምክር ቤቱ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በሚካሔደው 35ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይም ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።
በ40ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የምስራቅና ደቡብዊ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ዋና ጸሀፊን ጨምሮ በረካታ ሚኒሰትሮች ቀደም ሲል የአህጉሪቱ መዲና ወደ ሆነችው አዲስ አበበ መግባታቸው የሚታወስ ነው።