ፖለቲካ
በ50 ዓመታት የአየር ንብረት ልውጥ በዓለም ላይ ያስከተለው ጉዳት በአሃዝ
2 ሚሊዮን ሰዎች በአየንብረት ለውጥ አደጋዎች ሳቢያ ሞተዋል፤ ከ4 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የኢኮኖሚ ኪራሳ ደርሷል
በአፍሪካ ብቻ በ50 ዓመታት 755 ሺህ ሰዎች ሲሞቱ፤ ከ185 ቢሊዮን በላይ ዶላር ደግሞ የኢኮኖሚ ጉዳት አድርሷል
የተባበሩት ምንግስታት በቅርቡ ይፋ ባደረገው ጥናት ባለፉት 50 ዓመታት ማለትም ከፈረንጆቹ 1970 እስከ 2021 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ ከ12 ሺህ በላይ አስከፊ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎች ተከስቷል።
በነዚህ አደጋዎች ምክንያትም ህይወታቸውን ያጡ ዜጎች ቁጥር 2 ሚሊዮን ሲደርስ 4 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ዶላር የኢኮኖሚ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።
በአፍሪካ ብቻ ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ 1 ሺህ 800 አስከፊ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎች ተከስቶው 755 ሺህ ህዝብ ሲሞት ከ185 ቢሊዮን በላይ ዶላር ደግሞ የኢኮኖሚ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።
አስከፊ ድርቅ፣ በጎርፍ መጥለቅለቅ ፣የአውሎ ነፋስ እና የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ የደረሱ የአየር ንብረት አደጋዎች ናቸው።