በጉባኤው ላይ የአየር ንብረት ጉዳቶች እና ካሳ ጉዳይ እልባት እንደሚያገኝ ይጠበቃል
ኮፕ28 የአየር ንብረት ጉባኤ ለአፍሪካዊያን የተለየ ጥቅም እንደሚያመጣ ተገለጸ።
የዘንድሮው ዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የፊታችን ህዳር በተባበሩት ዓረብ ኢምሬት ዱባይ ይካሄዳል።
በዚህ ጉባኤ ላይ የሀገራት መሪዎች፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች፣ ተመራማሪዎች እና ኩባንያዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
በዚህ ጉባኤ ላይ ከሚሳተፉት መካከል አንዱ የሆኑት አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ የደረሰባትን ጉዳት ለማካካስ እየተደራደሩ ያሉት ኤፍሬም ሺቲማ እንዳሉት ኮፕ28 ለአፍሪካ ጠቃሚ መድረክ ነው ብለዋል።
ሺቲማ አክለውም ይህ ዓለም አቀፍ መድረክ ምንም በካይ ጋዝ ባትለቅም ከየትኛውም አህጉር በላይ እየተጎዳች ላለችው አፍሪካ ብዙ ጥቅም እንዳለው ተናግረዋል።
አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በትንሹ 86 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል ያሉት ቺቲማ ይህ የሚሆነው ግን የበለጸጉ ሀገራት ላደረሱት ጉዳት ካሳ የሚከፍሉበት አሰራር እና ህግ በጉባኤው ላይ ከጸደቀ መሆኑንም አክለዋል።
ቺቲማ አክለውም አፍሪካ ወደ ካባቢ አየር ከሚለቀቀው በካይ ጋዝ ውስጥ ያላት ድርሻ አራት በመቶ ብቻ ነው ብለዋል።
በኮፕ28 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የአፍሪላን እና የሌሎች ታዳጊ ሀገራትን ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር ልዩ መድረክ እንደሚሆንም ቺቲማ ከዓልዐይን ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ወቅት ተናግረዋል።