በደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናትን አግተው የነበሩ 56 የቀድሞ ወታደሮች ተያዙ
ወታደሮቹ እያንዳንዳቸው 4.2 ሚሊዮን የደቡብ አፍሪካ ራንድ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል
ታጋቾቹን ለማስለቀቅ የተደረገው ድርድር ባለመሳካቱ ፖሊስ የራሱን ጥበብ ተጠቅሞ ታጋቾቹን ማስለቀቁን ጉንጉበሌ ተናግረዋል
የነጻነት ጦርነት አርበኞች፣የመከላከያና የቀድሞ ወታደሮች ሚኒስትር ታንዲ ሞዲሴ እና ምክትላቸው ታባንግ ማክዌልታና በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያሉ ሞንድሊ ጉንጉብሌ ከስብሰባ እንዳይወጡ አግተዋቸዋል፡፡
ስብሰባው ከደብብ አፍሪካ ዋና ከተሞች አንዷ በሆነቸው ፕሪቶሪያ በቀድሞ ወታደሮች ፍላጎት ጉዳይ የሚመክር እንደነበረ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
የቀድሞ ወታደሮች በጸረ-አፓርታይድ ወቅት በተለያየ ወታደራዊ ቡድን ውስጥ ሆነው የታገሉ ሲሆኑ እያንዳንዳቸው 4.2 ሚሊዮን እንዲሰጣቸው በአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ፊት ለፊት ወጥተው ሰልፍ አድርገው ነበር፡፡
ጉንጉበሌ እንደገለጹት ቡድኑ ከፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ እና ከምክትል ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማቡዛ በስተቀር ከማንም ጋር ለመደራደር ፈቃደኛ አለመሆኑን ገለጾ ሚኒስትሮቹ እንዳይወጡ ለማድረግ ሁሉንም በሮች ቆልፈዋል።
ጉንጉበሌ ችግሩ “በፀጥታ ኃይሎች በጣም ውጤታማ እና በተሳካ ሁኔታ ተቀልብሷል፤… ሕጉ የዚህን ችግር ባህሪ በሚመለከት ረገድ ይፈታዋል ብለን እንጠብቃለን” ብለዋል።
ታጋቾቹን ለማስለቀቅ የተደረገው ድርድር ባለመሳካቱ ፖሊስ የራሱን ጥበብ ተጠቅሞ ታጋቾቹን ማስለቀቁን ጉንጉበሌ ተናግረዋል፡፡
በነፍስ አድን ወቅት የተኩስ ድምጽ የለም ”ሲሉ የፖሊስ ቃል አቀባይ ቪሽ ናኢዱ አርብ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። መግለጫው “ሰባት ሴቶችን ጨምሮ ቢያንስ 56 ሰዎች ተይዘዋል ፣ ቢያንስ በሦስት የአፈና ክሶች ክስ ሊመሰረትባቸው ይችላል” ብሏል መግለጫው፡፡