የጃኮብ ዙማን እስር ተከትሎ ደቡብ አፍሪካ በተፈጠረው ሁከት የሟቾች ቁጥር 337 ደርሰ
በሀገሪቱ ሁከቱ የተቀሰቀሰው በቀድሞው ፕሬዘዳንት እስር ምክንያት ነው
በእስር ላይ የነበሩት የቀድሞው ፕሬዘዳንት ዙማ ከእስር ወጥተው በወንድማቸው የቀብር ስነ-ስርአት ላይ እንዲገኙ ተፈቅዶላቸዋል
በቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ዳኮብ ዙማ እስር ምክንያት በተቀሰቀሰው ሁከት ምክንያት እስካሁን የ337 ሰዎችን ሕይወት መጥፋቱን መንግስት ማስታወቁን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ክቡድዞ ንፅሃኸኒ “የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ በጋውቴን ግዛት ውስጥ የሟቾችን ቁጥር 79 ሲሆን የሁከቱ ማእከል ተደርጋ በምትወሰደው ክዋዙሉ-ናታልን እስካሁን 258 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፡፡
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ የሙስና ጥያቄን ችላ በማለታቸው የ 15 ወር እስራት ከተላለፈባቸው አንድ ቀን በኃላ በተከሰተው ሁከት በሰዎች ላይ ከደረሰው በተጨማሪ በሲዎች በሚቆቱ የንግድ ድርጅቶች ላይ የዝርፊያና የማውደም አደጋ ተከስቷል፡፡
ፕሬዝዳንት ሲረል ራማፎሳ ሁከቱ ከአፓርታይድ ስርዓት ማብቂያ ወዲህ ወደ አስከፊው አመፅ ነው ብለውታል፡፡
እስካሁን ድረስ በግምት 3.4 ቢሊዮን ዶላር ግምት ያለው ንብረት ወድሟል፡፡ የዙማ የትውልድ ግዛት በሆነችው በኩዙሉ-ናታል እና በጋውንግ በተባሉ ሁከት የተስፋፋባቸው ሁለት አውራጃዎች የደቡብ አፍሪካን የኢኮኖሚ ምርት ግማሽ ያህሉን ይይዛሉ ፡፡
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ከእስር ቤት ወጥተው ከቀናት በኋላ በህመም ምክንያት በሞተው ወንድማቸው ማይክል የቀብር ሥነ-ስርዓት ላይ እንዲገኙ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ የሬዲዮ ዲጄን ጨምሮ ስድስት ሰዎች እስካሁን ድረስ በህዝባዊ አመፅ በማነሳሳት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል ፡፡
የሀገሪቱ ፖሊስ በርካታ ሺዎችን በዝርፊያና በማቃጠ ተሳትፈዋል በሚል ጥርጣሬ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡